የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ያገለገሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ያገለገሉ የተለያዩ ንብረቶች የግልፅ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
- ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት የመኪና መለዋወጫ ዕቃወች:
- የተለያዩ አይነት ያገለገሉ የቢሮ እቃዎች ፡ቁርጥራጭ እንጨቶች
- የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች፡
- የተለያዩ አይነት ቶነሮች፡ያገለገሉ የመኪና ባትሪ፤የተለያዩ ጀሪካኖች ፤
- ለስላሳ መጠጦች፤ቬንትሌተሮች እና ያገለገሉ በሮች፤በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ተጫራቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ከጨረታ ሰነዶች ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
1. የእቃዎቹ ዓይነትና ዝርዝር በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ አስር /10/ ቀናት ውስጥ ጨረታ ሰነዱን በጉርድ ሾላ ሳለተ ምህረት ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ ከሚገኘው ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኘት የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ በብር /800/ ስምንት መቶ ብር/በመግዛት የጨረታ ሰነዳችሁን እስከ ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
2. የእቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት የሚፈልጉ በጉርድ ሾላ ሳለተ ምህረት ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ የሚገኘው በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በግምጃ ቤት በመገኘት ጨረታው በሪፖርተር በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቶች ብቻ መጎብኘት ይችላሉ።
3.ተጫራቶቸ ከጨረታው በኋላ የሚመለስ የጫረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ /2%/ በCPO/ወይም ባንክ ጋራንቲ አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ገዥዎች የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎኘ እስከ ጨረታ መዝግያ ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. 8፡00 ሰዓት ተዘገቶ በእለቱ 8፡30 በጉርድ ሾላ በሚገኘው ሳለተ ምህረት በ/ክ ፊት ለፊት ድርራ ሞለ አጠገብ በሚገኘው የማኀበሩ መሰብሰበያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
5. ተጫራቶች ጨረታውን አሸናፊ መሆናቸው ከተገፀላቸው ተጫራቾች የሸነፋትን ንብረት ሙሉ ክፍያውን በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍለው ማንሳት ይኖርበቸዋል፡፡ ካልሆነ ግን ጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ /Cpo/ድርጅቱ ገቢ ያደርጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም።
6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ ከዚህ በታች በተጠቀሰዉ አድራሻ ስልክ በመደወል ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር
አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት
ስልክ ቁጥር፡ 011-515-06-08
ፖስታ ሳጥን ቁጥር፡ 41076
Tender details
- Deadline: 2026-06-26
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-06-26 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Red Cross Society
- Buyer address: ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሀይቅ ዳር ክ/ከተማ ጉዱ ማይሌ ቀበሌ ከዋና ማ/ቤት ጀርባ በኩል ነው።
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 800 (ስምንት መቶ ብር)
- Published: Jun 17, 2026
- Posted at: 2026-06-17T07:56:36.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.