ኦሮሚያ ኢንሹራንስ አ.ማ. የሙሉ ውድመት ካሳ ክፍያ ፈጸሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች እና የተሽከርካሪ አካላት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ቅዳሜ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን የሙሉ ውድመት ካሳ ክፍያ ፈጸሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች እና የተሽከርካሪ አካላት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ቅዳሜ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ለመሸጥ ይፈልጋል
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ተሽከርካሪዎቹ እና ሌሎች ቁሳቁሶች በሚገኙበት ቃሊቲ ሽዋ ዳቦ ጀርባ ሰለሞን ብሎኬት ማምረቻ አጠገብ በሚገኘው የኩባንያችን ሪከቨሪ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በወትር በስራ ሰዓት እስከ ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓም በመመልከት የሚመረቱበትን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ቦሌ ወሎ ሰፈር ወደ ወንጌላዊት ብምንጻ በሚወስደው መንገድ ተሊ ማሰልጠኛ አስፍ ብሎ ሊዲያ አስናቀ ህንፃ ላይ በሚገኘው ጥና መቤታችን 2ኛ ፎቅ በመግዛት ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ሰኔ 18 እና ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ ገቢ በማድረግ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ፡-
- ጨረታው በኩባንያው ዋና መቤት 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የሥልጠና አዳራሽ ቅዳሜ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ የውስጥ ኦዲት አገልግሎት እና ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን፤
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
- ተጫራቾች ለተሽከርካሪ የሚጫረቱ ከሆነ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 15% ወይም በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት በባንክ ክፍያ ማስያዣ (CPO) በታሽገ ኢንቨሎፕ ከነዋጋው ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሊሆን፤ የተሽከርካሪ አካላት የሚጫረቱ ከሆነ የጨረታ መነሻ ዋጋቸውን መሠረት በማድረግ ኩባንያችን ባስቀመጠው ዝርዝር መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ማስያዝ ይኖርበታል።
- ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ ከጨረታው በፊት ዕዳ ቢኖር በኩባንያው የሚሸፈን ይሆናል። ሆኖም ግን ከጨረታ በኋላ ያሉትን ማንኛውንም ወጪዎች በሙሉ ገዢው ይሸፍናል።
- የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪ ይከፍላሉ።
- አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት በኩባንያው የማስታወቂያ ቦርድ እና ድረ ገጽ ላይ የሚገለጽ ሊሆን፣ ውጤቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በአስር (10) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች ክፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል።
- የተለያዩ የተሽከርካሪ አካላት እና ቁሳቁሶችን የሚጫረቱ እና አሸናፊ የሚሆኑ በምድብ የተቀመጡትን ቁሳቁሶች ከኩባንያው የሪከቨሪ ግቢ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ወጪ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
- ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኦሮሚያ ኢንሹራንስ አ.ማ
ዋና መ/ቤት
አድራሻ፡- ቦሌ ወሎ ሰፈር ቴሌ ማሰልጠኛ አለፍ ብሎ ሊድያ አስናቀ ህንፃ
በስልክ ቁጥር 09 11 68 73 41/09 57 08 01 05 ወይም 0115-57-21-48
Tender details
- Deadline: 2026-06-26
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-06-27 09:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Insurance Company S.C.
- Bid bond: ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ 15%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jun 17, 2026
- Posted at: 2026-06-17T08:33:21.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.