አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ለአንድ ዓመት የሚቆይ የቀላል ተሽከርካሪ ኢንጀክሽን ፓምፕ፣ ኢንጀክተር ኖዝል፣ ሲሊንደር ሄድ እና ሲሊንደር ብሎክ የጥገና አገልግሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የብሐራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድ/ብግጨቁ/040/2018 ለአንድ ዓመት የሚቆይ የቀላል ተሽከርካሪ ኢንጀክሽን ፓምፕ፣ ኢንጀክተር ኖዝል፣ ሲሊንደር ሄድ እና ሲሊንደር ብሎከ የጥገና አገልግሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-
1. በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade Licensee)፣
2. በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢዎች ዝርዘር ውስጥ ስለመግባቱ በድረ-ገፅ የተመዘገበበት ኮፒ፣
3. የታክስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣
4 የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ (VAT) Certificate)፣
5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)፣
6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በማቅረብ በግልፅ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ።
በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት (6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት (ማዕከል) የግዥ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ወይም 7-01 መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡ 0116 663 206
አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-06-30
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-30 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Bus Service Organization
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Jun 18, 2026
- Posted at: 2026-06-18T07:58:55.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.