የጎንደር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን የቱርክ ብረት እና ጥቅል ሽቦ፣ ደብል ድራም ኮምፓክተር እንዲሁም ፕሌት ኮምፓክተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጎ/ከ/አስ/መንገዶች ባለስልጣን የ2018 ዓ.ም በጀት አመት
- ሎት 1 የቱርክ ብረት እና ጥቅል ሽቦ
- ሎት-2 ደብል ድራም ኮምፓክተር
- ሎት 3 ፕሌት ኮምፓክተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፣
1. የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው።
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ሚችሉ።
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና ሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ፊርማና ማህተም አድርገው አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት /ጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ አለባቸው።
6. ማንኛውም ተጫራች ለመግዛት የፈለገውን የጨረታ ሰነድ በጎ/ከ/አስ/መ/ባለስልጣን አዲሱ ቢሮ ቀበሌ 15 ሀዋርያጳውሎስ ታጥፎ ይዛኑ ሆቴል ገባ ብሎ በመምጣት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
7. ተወዳዳሪዎች ከሎት በላይ የሚወዳደሩ ከሆነ በሁሉም በሚወዳደሩባቸው ሎቶች CPO ማያያዝ ይኖርባቸው።
8. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው ከሎት1 - ሎት 3 ሰኔ 25/10/2018 ዓ.ም ሲሆን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-07-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-07-02 10:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Gonder City Roads Authority
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Jun 19, 2026
- Posted at: 2026-06-19T07:25:12.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.