በቂሊንጦ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል ለህብረት ሱቅ እና መዝናኛ ክበባት አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በቂሊንጦ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል ለህብረት ሱቅ እና መዝናኛ ክበባት አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን ማለትም የተፈጨ ቡና፣ የለውዝ ቅቤ፣ የሻይ ቅጠል፣ የዳቦ ዱቄት፣ የዳቦ እርሾ፣ የዳቦ ማኮፈሻ፣ ጨው፣ የምግብ ዘይት፣ የወጥ ማጣፈጫ ቅመም፣ ፕላስቲክ እሽግ ጁስ ባለ፣ ፕላስቲክ እሽግ ማር፣ እሽግ ውሃ፣ ኢንዶሚን፣ ወተት፣ እርጎ፣ ዱቀት ወተት፣ ገብስ ቆሎ፣ ማርማራታ፣ ማርጋሪን፣ የአሳ ሰርዲን የዶሮ ዕንቁላል፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ አፕል፣ ሙዝ፣ ማንጎ፣ አቮካዶ፣ ብርትኳን፣ ፓስታ፣ ማካሮኒ፣ አተር፣ ባቄላ፣ ምስር፣ ሩዝ፣ ዛላ በርበሬ፣ ቸኮሌት፣ ከረሜላ፣ ማስቲካ የገላ ሳሙና፣ የልብስ ሳሙና፣ ፈሳሽ ሳሙና፣ አይጃክስ፣ የዱቄት ሳሙና፣ የፀጉር ቅባት፣ የፊት ክሬሞች፡ ሎሽን፣ ቫዝሊን፣ ሻምፖ፣ ዶድራንት፣ የጥርስ ብሩሽ የጥርስ ሳሙና፣ የፂም መላጫ፣ የጥፍር መቁረጫ፣ ነጠላ ጫማ፣ ደብተር፣ እስክሪቢቶ፣ ልሙጥ ወረቀት፣ የሻይ ማሽን፣ የወንዶች የፀጉር ማሽን፣ የማቀዝቀዣ ፍሪጅ እና የመሳሰሉትን ሸቀጣ ሸቀጦች አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መመሪያና መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1, በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን፣ በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለፀ መሆን አለበት።
2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ።
3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
4. የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል አቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን የዘመኑን ግብር ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
5. ከደረጃ መዳቢዎች የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
6. ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
7. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ/ በኢትዮጰያ ንግድ ባንክ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል ስም በአካውንት ቁጥር 1000029497498 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 21 መግዛት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት።
9. ቴክኒካልና ፋይናንሽል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳደሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል።
10. ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገቡት ሰነድ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ቁጥር በትክከል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ሰነድ፤ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም።
11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲ ፒ ኦ ከቴክኒካል ሰነዶች ከኦርጅናሉ ጋር በአንድ ለይ አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
12. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000/ሀያ አምስት ሺህ ብር / በባንክ በተረጋገጠ CPO በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ስም አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሽገ ፖስታ እስከ ሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4:00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 21 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው እንዲሁም የባንክ ዋስትና የሚያስይዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆኑ ይኖርበታል።
13. ጨረታው ሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቂሊንጦ በሚገኘው በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።
14. ሆኖም ጨረታው! ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ ጨረታው አይስተጓጎልም ወይም ውድቅ አይሆንም።
15. የጨረታው ዝርዝር መመሪያ በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝሮ ቀርቧል።
16. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም እንዲሁም ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
17. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
18. ጨረታው በምከፈትበት ቀን የአመት በዓላት ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ጨረታው ይከፈታል።
አድራሻ፡ ቂሊንጦ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል አ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርስቲ አጠገብ
ለበለጠመረጃ፡- 011 452 2778 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል
ቂሊንጦ
ቂሊንጦ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል
Tender details
- Deadline: 2026-07-03
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-07-03 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Correctional Facility Kilinto
- Bid bond: 25,000.00 ብር
- Bid document price: 150.00 ብር
- Published: Jun 19, 2026
- Posted at: 2026-06-19T07:54:52.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.