የአ/ምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለመ/ቤቱ ለሠራተኞች አገልግሎት የሚሰጡ የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የአ/ምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለመ/ቤቱ ለሠራተኞች አገልግሎት የሚሰጡ የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡-
1ኛ. ሎት አንድ የደንብ ልብስ ዓይነቶች
2ኛ. ከላይ በቁጥር አንድ በተጠቀሰው የዕቃ ዓይነት የሥራ ዘርፍ ላይ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለ እንዲሁም በዘርፉ በቀጥታ ተሳታፈ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
3ኛ. ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የደንብ ልብስ አቅራቢ ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸውን የሚገልፅ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና የተጨማር እሴት ታክስ ተመዝጋብ መሆናቸውንና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TIN መኖሩን የሚገልጽ ማስረጃ ያለው።
4ኛ. ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ቀን የሚወዳደሩበትን የዕቃ ዓይነት ለእያንዳንዱ ዓይነት አንድ ሳምፕል ለውድድር ይዘው መቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
5ኛ. ተወዳዳሪዎች ሲያሸንፉ ወዲያውኑ ከድርጅቱ ጋር ውል ገብተው በራሱ ትራንስፖርት ወደ ድርጅቱ እስቶር አቅርቦ የጫኝና አውራጅ ችሎ ገቢ የሚያደርግ መሆን አለባቸው።
6ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች ብር 50,000/ሃምሳ ሺህ ብር/በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ cpo ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ዶክመንት ጋር ማስያዝ ይኖርበታል።
7ኛ. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር /ከፍሎ ከድርጅቱ በመውሰድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /በፖስታ/ ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናል ለብቻ ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒ ለብቻ እንዲሁም ፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናል ለብቻ ፋይናንሻል ዶክመንት ኮፒ ለብቻ አሽጎ ለጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአርባምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግቢ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በ8፡00 ሰዓት ተዘግተው በ8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።
8ኛ. በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።
9ኛ. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046 881 0369/ 046 881 2049 መደወል ይቻላል።
የአ/ምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-07-06
- Publishing entity: Arba Minch Town Water Supply and Sewerage Enterprise
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jun 20, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.