የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፍቹ ካምፓስ በ2019 ዓ.ም ከመንግስት በሚያገኘው በጀት ለእጩ መምህራን ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ አይነት እህል፣ ጥራጥሬ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ የባልትና ውጤቶች፣ የከብት ስጋ፣ ዳቦ፣ የማገዶ እንጨት እና ለወጥ ማጣፈጫነት የሚውሉ ግብአቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ተጫራቾችን በጋዜጣ ማስታወቂያ መጥራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር በሰሜን ሸዋ ዞን ፍቼ ከተማ የሚገኘው የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፍቹ ካምፓስ በ2019 ዓ.ም ከመንግስት በሚያገኘው በጀት ለእጩ መምህራን ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ አይነት እህል፣ ጥራጥሬ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ የባልትና ውጤቶች፣ የከብት ስጋ፣ ዳቦ፤ የማገዶ እንጨት እና ለወጥ ማጣፈጫነት የሚውሉ ግብአቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ተጫራቾችን በጋዜጣ ማስታወቂያ መጥራት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾቹ

1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ንግድ ፍቃዳቸው የታደሰና ከሚወዳደሩበት ዘርፍ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው መሆን አለበት።

3. ተጫራቾቹ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢን ቦንድ) 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው።

4. ተጫራቾቹ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል ከፍቼ መምህራን ት/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 13 መግዛት ይችላሉ።

5. ጨረታዉ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ5፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

6. ካምፓሱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራርያ፡- በስልክ ቁጥር፡- 0110351679/0111350969/0111350708/በመደወል ወይም ፍቼ መምህራን ት/ኮሌጅ በግንባር ቀርበው መረዳት ይችላሉ።

ኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፍቼ ካምፓስ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-08
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-08 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Oromia State University
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jun 20, 2026
  • Posted at: 2026-06-20T08:19:51.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders