የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹ የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨቁ 15/2018 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

/

 

ዘርፍ

 

የጨረታው ዓይነት

እቃው ያለበት ቦታ

1

የፅዳት ዕቃዎች

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ///ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን

2

አልባሳት

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ///ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን

3

ልዩ ልዩ ዕቃዎች

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ///ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን

4

ኤሌክትሮኒክስ

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ///ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን

5

ኮስሞቲክስ

ግልፅ ጨረታ

በሰመራ ///ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን

6

ፓኪንግ ማሽን

ሐራጅ ጨረታ

በሰመራ ///ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን

7

ያገለገሉ መገናኛ መሳሪያዎች

ሐራጅ ጨረታ

በሰመራ ///ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን

8

ጫማ

ሐራጅ ጨረታ

በሰመራ ///ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን

በመሆኑም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡-

1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ስብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ( ክሊራንስ) ማቅረብ ያለበት ሲሆን የሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት መነሻ መሸጫ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልገውም። በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለበት ሲሆን ለሐራጅ ጨረታ ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት ማቅረብ ይኖርበታል፤

2. የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ1፡00- 5፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ግቢ ውስጥ ውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

3. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና በሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ያገለገሉ መገናኛ መሳሪያዎች ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር)፤ ጫማ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) እና ፓኪንግ ማሽን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ለጨረታ ዋስትና (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ ስም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION SEMERA BRANCH OFFICE በሚል በባንክ አሰርተው ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰመራ እና ከሎጊያ ቅርንጫፎች ብቻ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ።

.

 

የቅ//ቤቱ ስም

 

የጨረታው አይነት

 

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ

የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ሰመራ /// ቤት

 

ግልጽ ጨረታ

 

እስከ 17/10/2018

 

18/10/2018 / 330 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 345 ሰዓት ይከፈታል

2

ሰመራ /// ቤት

 

ሐራጅ ጨረታ

 

እስከ 17/10/2018

 

18/10/2018 /ም 4፡00 ሰዓት ይከፈታል

5. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በሰመራ ጉ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ  ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።

6. ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል፡፡ ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።

8. ቅ/ጽ/ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን እቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው።

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. የዕቃውን ናሙና (sample) ሳያይ የሚጫረት ተጫራች ቅ/ፅ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑ ይታወቅ።

11. አሸናፊ ተጫራች ተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) 15% የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ።

12. ለተጨማሪ መረጃ በስ/ቁ፡-033 240 1510 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-25
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-06-25 10:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Afar
  • Publishing entity: Semera Customs Branch Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published: Jun 20, 2026
  • Posted at: 2026-06-20T09:00:07.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders