ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር ለምርት ስራ አገልግሎት የሚውል ሞዲፋይ ስታርች (Modify Starch) በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር WVD32/2017-oc

1) ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር ለምርት ስራ አገልግሎት የሚውል ሞዲፋይ ስታርች (Modify Starch) በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 2) በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከኣክሲዮን ማህበሩ ቅ/ጽ/ቤት አዲስ አበባ ወይንም ከዋናው መስሪያ ቤት ኮምቦልቻ መግዛት ይቻላል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በትክክል በመሙላት በሰም በታሸገ ፖስታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራቀናት ውስጥ በጨረታ መመሪያው ላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ, በ(CPO) ወይንም በባንክ ጋራንቲ በማስያዝ ኮምቦልቻ ዋናው መ/ቤት ወይም አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ፓፓሲኖስ ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 143 ወይም 144 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ማቅረብ ይችላሉ።

3) ጨረታው ማስታወቂያው በተዘጋ በ3ኛው ቀን ኮምቦልቻ (ወሎ) በዋናው መስሪያ ቤት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

4) ይህ ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።

5) አ/ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን መሉበሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡-

ስልክ ቁጥር-033-551 0627/551 0211/ 09 73 42 42 42(ኮምቦልቻ)

ስልክ ቁጥር-011-553 0124/551 3797/ 09 70 23 05 71(አዲስ አበባ)

ራስ ደስታ ዳምጠው ጎዳና ፓፓሲኖስ ሕንፃ አንደኛ ፎቅ

የኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-07-09
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ 9፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-11 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ማስታወቂያው በተዘጋ በ3ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Kombolcha Textile Share Company
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jun 21, 2026
  • Posted at: 2026-06-22T08:07:34.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders