አይናጌ ሕፃናት እና ቤተሰብ ልማት ድርጅት እ.ኤ.አ ከ ሐምሌ 2025 እስከ ሰኔ 30,2026 ድረስ ለ1 ዓመት አጠቃላይ ገቢና ወጪውን እንዲሁም የፕሮግራም አፈጻጸም ጥራቱን በውጭ ኦዲተር ማስመርመር/ ማሰራት ይፈልጋል
Description
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
አይናጌ ሕፃናት እና ቤተሰብ ልማት ድርጅት በኢፌዴሪ የሲቪል ማህረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን -በዳግም ምዝገባ ቁጥር 1544 ተመዝግቦ የሚገኝ በኢትዮጵያ ነዋሪዎች ድርጅት በማዕከላዊ አትዮጵያ በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ የተለያዩ የልማት ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው።
ስለሆነም እ.ኤ.አ ከ ሐምሌ 2025 እስከ ሰኔ 30,2026 ድረስ ለ1 ዓመት አጠቃላይ ገቢና ወጪውን እንዲሁም የፕሮግራም አፈጻጸም ጥራቱን በውጭ ኦዲተር ማስመርመር የሚፈልግ ሲሆን ከአሸናፊው የኦዲት ድርጅት ጋር ለ3 ዓመታት ውል ገብቶ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ማንኛውም የአዲት ድርጅት ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የኦዲተርነት የፍቃድ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
- የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
- ከፌዴራል ወይም ከክልል ኦዲት መ/ቤት ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
- ካሁን በፊት ባከናወኑዋቸው የኦዲት ስራዎች የመልካም ስራ አፈጻጸም ድርጅቶች ስለመስራታቸው የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ የሚችል።
በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች መረጃውን እና የምትሰሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቢሮአችን ድረስ በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ወይም አዲስ አበባ ቦሌ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ጀርባ በሚገኘው አጋር ድርጅታችን ቻይልድ ፈንድ ኢትዮጵያ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- አመታዊ በጀት፡ 66,397.710.00 ብር (ስልሳ ስድስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አስር ብር)
- የቦክስ ፋይል ብዛት - 45 (አርባ አምስት)
ማሳሰቢያ፡-
የኦዲት ድርጅቱ ለሚልከው ባለሙያ ማንኛውንም የምግብ፣ የአልጋ፣ የትራንስፖርት እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን በራሱ ይሸፍናል።
አድራሻ ስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ ቅበት ከተማ ከቦቤ ት/ቤት ፊት ለፊት (ከአዲስ አበባ ሆሳዕና በሚወስደው መንገድ ከቡታጅራ ከተማ 12 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ)
ስልክ ቁጥር፡- 0913381437 /0923281871
አይናጌ ሕፃናት እና ቤተሰብ ልማት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-06-30
- Publishing entity: Aynage Children and Family Development Organization
- Published: Jun 21, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.