መጋዘን ውስጥ የሚገኝ በጥቅል 50/ሀምሳ/ በግምት ሃያ አምስት ቶን የሚሆን 3 ሚሊ ሜትር ዲያሜትር ያለው የሽቦ ጨረታ ማስታወቂያ

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

  • አፈ/ከሳሽ አማራ ህንፃ ስራዎች ኮንስትራክሽን /ዘመን ኮንስትራክሽን /
  • አፈፃፀም ተከሳሽ፡ይፋት ትሬዲንግ ኃ / የተ / የግ/ ማህበር

መካከል ባለው የአፈፃፀም ክርክር ጉዳይ፤በባህርዳር ከተማ አፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ አዲስ አለም ቀበሌ ሸኔል ሆም የተገጣጣሚ ህንፃ ማምረቻ ፋብሪካ ከሚገኘው መጋዘን ውስጥ የሚገኝ የአፈፃፀም ተከሳሽ ንብረት የሆነ በጥቅል 50/ሀምሳ/በግምት ሃያ አምስት ቶን የሚሆን 3 ሚሊ ሜትር ዲያሜትር ያለው ሽቦ መነሻ ዋጋ በአንድ ኪሎ ግራም ብር 240/ሁለት መቶ አርባ ብር/ አፈ/ተከሳሽ ስም የተመዘገበውን ሽቦው በሚገኝበት አድራሻ በባህርዳር ከተማ አፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ አዲስ አለም ቀበሌ ሸኔል ሆም የተገጣጣሚ ህንጻ ማምረቻ ፋብሪካ ቅጥር ጊቢ ውስጥ በግልጽ ጨረታ ሐምሌ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ ጨረታ እንዲሸጥ የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ትዕዛዝ በሰጠው መሰረት የባህርዳር ከተማ አፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት አንድ ሰው ታዛቢ በመመደብ የባህርዳር ከተማ 5ኛ ፖሊስ ጽ/ቤትም ፀጥታውን የሚያስከብር አንድ ሰው በመመደብ የጨረታው ስነ-ስርዓት በአግባቡ እንዲከናወን እንዲደረግ ሆኖ የአብከመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሐራጅ ባይም ጨረታውን በበላይነት በመምራት ጨረታው ይካሄዳል።

ስለሆነም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ ማንኛውም ሰው ከቦታው በመገኘት ምልከታ አድርጐ ቀርቦ ህጋዊ መታወቂያ በመያዝ መጫረት መሳተፍ የሚቻል እና አሸናፊው እንደታወቀ ያሸነፈበትን ገንዘብ ከተቻለ ሙሉውን ገንዘብ የሚያስይዝ ካልተቻለም አንድ አራተኛውን ወዲያውኑ ማስያዝ የሚችል መሆኑን እንዲያውቁት የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት አዟል።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-13
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-07-13 12:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara National Regional State Supreme Court
  • Published: Jun 21, 2026
  • Posted at: 2026-06-22T08:14:14.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders