አዋሽ ባንክ አ.ማ. ያገለገሉ ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ ንብረቶች የጨረታ ማስታወቂያ

አዋሽ ባንክ አ.ማ. ሲጠቀምባቸው የነበሩትን

  • 10 ተሽከርካሪዎች በሎት (1) እና 
  • በሎት (2) (ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ስካነር፣ ቼክ ስካነር፣ ላፕቶፕ፣ የብር መቁጠሪያ፣ መፈተሻ ማሽን፣ የሂሣብ መደመሪያ፣ የዶላር መፈተሻ ማሽን፣ ፋክስ፣ ፎቶ ኮፒ፣ የውሃ ማጣሪያ፣ ቴሌቭዥን፣ ታይፕራይተር፣ የሙቀት መለኪያ፣ ቬንትሌተር፣ ብሎወር፣ ቴፕ ሪከርደር፣ የተለያዩ ባትሪዎች፣ ዩፒኤስ፣ ስታብላይዘር፣ እሳት ማጥፊያ፣ ወረፋ መጠበቂያ፣ የተለያዩ ወንበሮች፣ ኤ ቲ ኤም ሼልተር፣ የጥበቃ ቤት፣ ፍራሽ አሉሚኒየም ፓርቲሽን፣ የተለያዩ የማስታወቂያ ምልክቶች፣ በሮች፣ መጋረጃ፣ የተለያዩ ንቃይ ቆርቆሮዎች፣ ብረታ ብረቶች፣ የአምፖል ማቀፊያ፣ መስታወት፣ የተለያዩ ገመዶች፣ ካውንተር ዴስክ፣ የተለያዩ ጠረጴዛዎች፣ የኮት መስቀያ፣ የብረት መደርደሪያ፣ የውሃ ማጠራቀሚያ(ሮቶ) የመጽሐፍ መደርደሪያ፣ ፋይሊንግ ካቢኔት፣ ላተራል ፋይሊንግ ካቢኔት፣ እምነበረድ፣ ካርቶን፣ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እና ጎማዎች) ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚቻል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፤-

1. ስለ ጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር መረጃ የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ) በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በሂሣብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ደረሰኙን አዋሽ ባንክ ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል የቢሮ ቁጥር M-11 በመቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማስገባት ይችላሉ፣

2. ተጫራቾች በሎት 1 ላይ ለተገለጹት ተሽከርካሪዎች በባንኩ የተቀመጠውን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር ስም አሰርቶ ማስገባት ይኖርበታል፣

3. በሎት 2 ላይ ለተዘረዘሩት የቢሮ መገልገያ ንብረቶች ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ንብረት ያቀረቡትን ዋጋ 1/4ኛ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር ስም አሰርቶ ማስገባት ይኖርበታል፣

4. ያለ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፣

5. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) 15%፣ ለተሽከርካሪዎቹ የስም ማዘዋወሪያ፣ የተሽከርካሪ የዋጋ ግምት፣ በጨረታ ዋጋ እና የመንገድ ትራንስፖርት ባለሞያ ግምት መካከል ሊፈጠር የሚችለውን የተ.እ.ታ. የዋጋ ልዩነት ገዥ ይሸፍናል፣

6. ንብረቶቹን አሸዋ ሜዳ በሚገኙት የባንኩ መጋዘኖች እንዲሁም ተሽከርካሪዎቹን በተመለከተ ልደታ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ባልቻ ሳፎ ሕንጻ በአካል ቀርበው እና የገዙትን የጨረታ ሰነድ በመያዝ በወጣው ፕሮግራም መሠረት መጐብኘት ይቻላል፣

7. ጨረታው ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል የቢሮ ቁጥር M-11 ውስጥ ይከፈታል፣ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፣

8. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ከፍያ ፈጽሞ ንብረቶቹን መረከብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ለባንኩ ገቢ በማድረግ ጨረታው ይሰረዛል፣

9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

10. ስለ ጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር ማብራሪያ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀን በፊት በስልክ ቁጥር 0115-30 30 14 /0115-576815/ 0115-303026 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

አዋሽ ባንክ አ.ማ.


Tender details

  • Deadline: 2026-07-08
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-07-08 10:10
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Awash Bank Share Company
  • Bid bond: በየሎቱ 25%
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 21, 2026
  • Posted at: 2026-06-22T08:27:33.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders