የኦሮሚያ መንገዶችና ሎጂስቲክስ ቢሮ የተለያዩ ዓይነት ተሽከርካሪዎችን የጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውሉ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሙሉ አቅም ያለው ጋራዥ አወዳድሮ በኮንትራት ውል መግባት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የጋራዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ኦ.መ.ሎ. ቢ 33/2018
የኦሮሚያ መንገዶችና ሎጂስቲክስ ቢሮ (ኦ.መ.ሎ ቢ) ከዚህ በታች የተገለጹትን የቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችን ለአንድ ዓመት በኮንትራት ፍሬም ዎርክ ውል የተለያዩ ዓይነት ተሽከርካሪዎችን የጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውሉ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሙሉ አቅም ያለው ጋራዥ አወዳድሮ በኮንትራት ውል መግባት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ
1ኛ. ሎት 1 :- የቀላል ተሽከርካሪዎችን ጥገና ሥራ አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 200,000.00
2ኛ. ሎት 2 :-የከባድ ተሽከርካሪዎችን ጥገና ሥራ አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 200,000.00
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፤
2. ወቅታዊ የመንግሥት የግብር ግዴታውን ስለመወጣቱ የሚያመለክት ደብዳቤ ከገቢዎች መ/ቤት
3. የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያመለክት ሰርተፊኬት፤
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያመላክት
5. ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚገልጽ /TIN/ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተጠቀሱትን ሠነዶች ፎቶ ኮፒ ከማመልከቻ ጋር አያይዞ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ከሣር ቤት ወደ ቄራ በሚወስደው በስተቀኝ መንገድ ላይ በተሰራው የኦሮሚያ ክልል መንግስት ሕንፃዎች ውስጥ በጨፌ ኦሮሚያ ሕንፃ አጠገብ ቢሮው መ/ቤት ሆኖ 3ኛ ፎቅ ከሚገኘው የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በዝርዝር የተመለከተውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ከላይ በተገለፀው መሠረት ማስያዝ አለባቸው።
8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት ድርጅቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሐምሌ 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው በዚሁ ዕለት ማለትም ሐምሌ 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ በተጠቀሰው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።
10. ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ መንገዶችና ሎጂስቲክስ ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-07-09
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-07-09 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Roads and Logistics Bureau
- Bid bond: በየሎቱ 200,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jun 21, 2026
- Posted at: 2026-06-22T09:01:23.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.