ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ያገለገሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ግልጽ ጨረታ

የጨረታ መለያ ቁጥር ንብ/74/2018

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ያገለገሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የዕቃዉ ዓይነት

መለኪያ

መግለጫ (ማብራሪያ)

1

ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች

በኪሎ ግራም

ተመዝኖ የሚታወቅ

2

አሉሙኒየም ፕሮፋይል

በቁጥር

ቁመታቸው 7 ሜትር የሚሆን

3

አሉሙኒየም ፕሮፋይል

በቁጥር

ቁመታቸው 4.2 ሜትር የሚሆን

  1. ጨረታው በባንኩ የግዢ መምሪያ ላይ በተጠቀሰው የግልጽ ጨረታ ሃደት መሰረት ይከናወናል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00/ብር ሁለት መቶ/ በንብ ባንክ አካውንት ቁጥር ETB1764600010001 በቅድሚያ በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፎች ላይ በመክፈል የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ከሰኔ 17, ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 - 6፡00 ሰዓት እና ከ7፡00-11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ሰነዱን ገርጂ ኢምፔሪያል ጀርባ በሚገኘው የባንኩ ዋና ዕቃ ግምጃ ቤት በመገኘት መውሰድ ይችላሉ።

3. በሎት ሁለት ለተዘረዘሩት ዕቃዎች ተጫራቾች ዕቃዎቹን ፈጭተው ወይም የይዘት ለዉጥ አድርገዉ መጠቀም የሚችሉ ከሆነ መወዳደር ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ የተጠቀሱትን ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ ለመመልከት የጨረታ ሰነዱን የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ ከሰኔ 17, ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ 2፡00 - 6፡00 ሰዓት እና ከ7፡00-11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ድረስ ዕቃዎቹን ገርጂ ኢምፔሪያል ጀርባ በሚገኘው የባንኩ ዋና ዕቃ ግምጃ ቤት እና ሰንጋ ተራ በሚገኘው የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ቤዝመንት በመገኘት ማየት ይችላሉ።

5. ተጫራቶች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከታች በተራ ቁጥር 8 ስር በተጠቀሰው አድራሻ እስከ ሐምሌ 07 ቀን 2018 ዓ.ም. ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።ዘግይቶ የደረሰ የመወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

6. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ አጠቃላይ ብር 100,000.00 (ብር አንድ መቶ ሺህ) በሲፒኦ ከዋናው የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው ማቅረብ አለባቸው።

7. ከላይ የተዘረዘሩት የሚሸጡ ዕቃዎች ላይ የተ.እ.ታ ይታሰባል።

8. ጨረታው ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 9፡15 ሰዓት ሰንጋ ተራ በሚገኘው ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ 26ኛ ፎቅ ግዢ ዋና ክፍል ውስጥ ይከፈታል።

9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ

ስልክ ቁጥር፦ 011 629 6246 / 011 551 2650 ፋክስ 011 562 2448


Tender details

  • Deadline: 2026-07-24
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid opening: 2026-07-24 15:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Nib International Bank S.C.
  • Bid bond: 100,000.00 (ብር አንድ መቶ ሺህ)
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jun 21, 2026
  • Posted at: 2026-06-22T10:03:49.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders