በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት በከተማ ውስጥ ከሚገኙ ጋራዦች የተሽከርካሪ ዓመታዊ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 01/2019

በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት በከተማ ውስጥ ከሚገኙ ጋራዦች የተሽከርካሪ ዓመታዊ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባችኋል።

1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ አግባብነት ያለውና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ ዌይብ ሳይት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ከዌይብ ሳይት አትመው ከጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ የሚችሉ ወይም በክልሎች በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የግዥው መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል።

5. ተጫራቾች ጨረታው ከፍት ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ በቢሮው የተዘጋጀውንና የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ የንግድ ፈቃዳቸውን በማሳየት ዘወትር በሥራ ሰዓት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቀርበው የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድና የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በአግባቡ በማዘጋጀት በፖስታ አሽገው ጨረታው ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ቀን እስከ 11፡25 ሰዓት ድረስ በቢሮው ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት የመጨረሻው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ቀጥሎ ባለው 16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ይከፈታል። 15ኛው እና 16ኛው ቀን የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ቀን ላይ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ3፡00 ሰዓት ተዘግቶ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል።

7. ተጫራቾች የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ስም ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 30,000.00 በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

8. የፋይናንሻል የቴክኒክ ሰነድ እና የሲ.ፒ.ኦ ፖስታ ተለይቶ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው አየር ላይ መቆያ ጊዜ ከሚያበቃበት የመጨረሻው ቀን ጀምሮ ላሉት ለ60 ተከታታይ ቀናት የሚያገለግል መሆን ይኖርበታል።

9. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት በ05 ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በመያያዝ በ15 ቀናት ውስጥ ውል መግባት የሚችሉ መሆን አለበት።

10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-180-5071 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-08
  • Publishing entity: Southern Ethiopia Regional State Finance Bureau
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jun 21, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders