ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. ጉዳት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ተገቢውን ካሣ ከፍሎ በውክልና የተረከባቸውን ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ የተሽከርካሪ አካሎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 158/2018)
ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አማ
NILE INSURANCE COMPANY S.C
ጉዳት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ተገቢውን ካሣ ከፍሎ በውክልና የተረከባቸውን ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ የተሽከርካሪ አካሎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
የተሽከርካሪ የስም ማዛወሪያ፣ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ግብርና ሌሎች ዕዳዎችና ወጪዎች ቢኖሩ በአሸናፊው የሚሸፈኑ ይሆናል።
የተሽከርካሪ የስም ዝውውር በገዢ ምክንያት ከስድስት ወር በላይ ቢቆይ በዚህ ምክንያት ለሚመጣ ችግር ኩባንያችን ኃላፊነት አይወስድም።
አሸናፊ ተጫራች የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማቅረብ ይኖርበታል።
1. ንብረቶቹ የሚገኙበት የኩባንያው ሪከቨሪ አድራሻ፡-
ገላን ሪከቨሪ ፡ ገላን ኖክ ፊት ለፊት
ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ በሥራ ሰዓት ሄዶ በማየት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ከፍሉ መውሰድ ይችላል።
የጨረታ መነሻ ዋጋ 15% ቫት ያላካተተ መሆኑን እየገለጽን፣ ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን የእያንዳንዱን ምድብ እቃ ዋጋ (ቫት ሳይጨምር) በጨረታ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት ለእያንዳንዱ ምድብ እቃ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋውን 20% (ሃያ ከመቶ) በኩባንያው ስም በተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የኢንሹራንስ ቦንድ ጋር በኤንቨሎፕ በማሸግ እስከ ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ብቻ የኩባንያው ዋና መ/ቤት በሚገኝበት ብሔራዊ ቲያትር ከንብ ባንክ ቀጥሎ ባለው ህንፃ ምድር ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል።
ማሳሰቢያ፡- አሸናፊ ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ 15% ቫት የሚጨመር መሆኑን እንገልፃለን።
ጨረታው ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ብሔራዊ ቲያትር ከንብ ባንክ ቀጥሎ ባለው ህንፃ በኩባንያው ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ 21ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4 እና 5 ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ይከፈታል።
ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ሙሉ በሙሉ የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ከሚገዙበት ዋጋ ጋር ይታሰባል። ተጫራቾች ለተጫረቱበት ንብረት አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በአሥር ቀናት ውስጥ ክፍያውን አጠናቀው ንብረቱን ባያነሱ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል።
ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር 011 140 7171/09-11-82-05-76/ በመደወል መጠየቅ ይችላል።
ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-06-26
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-06-27 09:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Nile Insurance Company S.C.
- Bid bond: 20% ለእያንዳንዱ ምድብ እቃ
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published: Jun 21, 2026
- Posted at: 2026-06-22T11:58:36.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.