በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የባቱ ኮስቲክ ሶዳ ፋብሪካ በፋብሪካው ዋና ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሚወገዱ ንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 002-2018

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የባቱ ኮስቲክ ሶዳ ፋብሪካ በፋብሪካው ዋና ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙትን

  • የተለያዩ ብረታ ብረቶችን፣አንድ ደብል ካፕ ሚትሱቢሽ ተሽከርካሪ፣ሁለት የሲሚንቶ ወፍጮ ሴፓሬተሮችን፣
  • የውሃ ማጠራቀሚያ ማከማቻ ታንከር ማይዝግ ፣ያገለገሉ ጎማዎች ፣አንድ አዲስ የትራክተር ጎማ፣
  • የኬሚካል መከላከያ ሸክላዎችን፣ የወረቀት ማሸጊያ ከረጢቶችንና የብረት ዝገት መከላከያ ቀለም እና 
  • ያገለገሉ ፍሪጆችን እና የተለያዩ በጣውላ የተሰሩ ስብራባሪ ወንበሮችን ፣ጠረጴዛዎች እና
  • መደርደሪያዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች አሟልቶ መወዳደር ይችላል።

1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና ለግብር ከፋይ የሚሰጥ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ባቱ ከተማ ካለው የፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ከኩዌት ኤምባሲ 10 ሜትር ገባ ብሎ ናሚቢያ ወይንም ጅቡቲ ኤምባሲ ፊትለፊት ከሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር ሶስት መቶ (300.00) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድና የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ንብረቱ የሚገኝበት ባቱ(ዝዋይ) ከተማ ፋብሪካው ቅጥር ግቢ ድረስ በመገኘት መመልከት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 3 በመቶ(3%) በባቱ ኮስቲክ ሶዳ ፋብሪካ ስም የተዘጋጀ የባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ናሚቢያ ጂቡቲ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ማርኬቲንግ ማስተባበሪያ ቢሮ ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻው ቀን በዓል ወይንም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

6. የጨረታው አሸናፊዎች ተለይቶ እንደታወቁ ያሸነፉበትን ዋጋ ቀርበው ከከፈሉ በኋላ በአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ በራሳቸው ተሽከርካሪ ማንሳት ይጠበቅባቸዋል።

7. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ
አ.አ ስልክ ቁጥር 011-618 4310/17
አ.አ ፋክስ ቁጥር 011-618-1529
ባቱ ስልክ ቁጥር 046-441-3415
ባቱ ፋክስ ቁጥር 046-441-2463
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የባቱ
ኮስቲክ ሶዳ ፋብሪካ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-07
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-07 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Chemical Industry Corporation
  • Buyer address: ቦሌ ሩዋንዳ ናሚቢያ/ጅቡቲ ኤምባሲ ፊት ለፊት
  • Bid bond: 3%
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 22, 2026
  • Posted at: 2026-06-23T07:30:30.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders