በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የተለያዩ አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር መኢኢግ/ኤኢኢ/001

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የተለያዩ አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትጫረቱ በአክብሮት ተጋብዟችኋል።

.

የእቃዎች ዝርዝር

ሎት

የጨረታ ማስከበሪያ በብር

1

የተለያዩ ያገለገሉ የእንጨት ውጤቶች (Furniture Products)

1

5,000.00

 

2

የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች (Different Types Metal products)

2

19,000.00

 

3

የቴሌቪዥን አክሰሰሪዎች (TV Accessories)

3

21,300.00

 

4

የተለያዩ አይነት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች (Vehicles)

4

45,000.00

 

5

ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ፣ ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን

5

3,000.00

 

6

የተለያዩ አይነት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

6

8,000.00

 

7

የሞባይል አክሰሰሪዎች (Mobile Accessories)

7

58,000.00

 

Grand Total

 

 

159,300.00

 

1. ዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin) ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ሎት ወይም ለሁሉም ሎቶች ለብቻው በፖስታ አሽገው ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል በመሙላትና በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው።

6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት።

7. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመከላከከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ በኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ከአቅርቦት መምሪያ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 (ሰላሳ ቀናት) ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለገጣፎ ቅርንጫፍ በኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ አካውንት ቁጥር 1000692062144 ገቢ በማድረግ ሰነዱን መውሰድ ትችላላችሁ።

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 (ሰላሳ ቀናት) አየር ላይ ውሎ በ31ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይዘጋል። በዚሁ ዕለትም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንዱስትሪያችን በዲዛይን አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

10. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።

11. ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ 45 (አርባ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ስለሆነ ተጫራቾች ይህን አውቀው የዋስትና ጊዜው ጨረታው ኪሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።

12. ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም። ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

13. አድራሻ፡- በሸገር ከተማ ኩራ ጂዳ ክፍለ ከተማ 44 ማዞሪያ ለገዳዲ ውሃ ማጣሪያ ግድብ አጠገብ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡ በስልክ ቁጥራችን 09 13 84 62 79/ 09 10 27 43 08 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-22
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ለተከታታይ 30 (ሰላሳ ቀናት) አየር ላይ ውሎ በ31ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-22 12:00
  • Bid opening (note): ለተከታታይ 30 (ሰላሳ ቀናት) አየር ላይ ውሎ በ31ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 22, 2026
  • Posted at: 2026-06-23T08:06:51.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders