በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ፋይናንስ ስራ አመራር ዘርፍ የሚገኙትን የተለያዩ ያገለገሉ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ አካላት፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ የተሽከርካሪ ጎማዎች እና ባትሪዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፤ ቁርጥራጭ ብረታብረቶች፤ የተሽከርካሪ አካላት፣ ጎማዎች እና ባትሪዎች ለመሸጥ የወጣ ጨረታ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ፋይናንስ ስራ አመራር ዘርፍ የሚገኙትን የተለያዩ ያገለገሉ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ አካላት፣ ቁርጥራጭ ብረታብረቶች፣ የተሽከርካሪ ጎማዎች እና ባትሪዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ በሚገኘው መከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ግቢ ውስጥ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ፣ የተሽከርካሪ አካላት፣ ቁርጥራጭ ብረታብረቶች ፣ የተሽከርካሪ ጎማዎች እና ባትሪዎች ሠነድ የጨረታ መለያ ቁጥር መከ/ንብ/አስ/01/2018 የማይመለስ (ለተሽከርካሪ) ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) የጨረታ መለያ ቁጥር መከ ንብ/አስ/02/2018 የተሽከርካሪ አካላት ፣ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ የተሽከርካሪ ጎማዎች እና ባትሪዎችን የማይመለስ ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪዎችለመሸጥየተቀመጠውን መነሻ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) [Ministry of Defense Property Sales Saving Account ፣ የተሽከርካሪ ጎማዎችና ባትሪዎች ለመሸጥ የተቀመጠውን ጠቅላላ ዋጋ (ሁለት በመቶ) 2% |Ministry of Defense Property Sales Saving Account/ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ንብረት ሽያጭ ማጠራቀሚያ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ተሞልቶ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 የስራ ቀናት የሚሸጡ ተሽከርካሪዎችን ለማየት ኮፈን ተከፍቶ ስለሚቆይ ዘወትር በስራ ሠዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡00 ሠዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ደ ዘይት ( ቢሾፍቱ በሚገኘው አውቶሞቲቭ ካምፕ ጀርባ እና አየር ሃይል ግቢ)፣ ሃዋሳ (ቶጋ ካምፕ)፣ነቀምት(ዴዴሳ ካምፕ)ሃረር(ምስራቅ ዕዝ ትራንስፖርት መምሪያ፣ ባህር ዳር (መኮድ ካምፕ)፣ አዳማ (አዳማ ጋርመንት)፣ አዲስ አበባ 4ኛ ክ/ጦር ሲሆን ቁርጥራጭ ብረታብረቶች፣ የተሽከርካሪ አካላት፣ የተሽከርካሪ ጎማዎች እና የተሽከርካሪ ባትሪዎች በተመለከተ ከላይ ከተገለፁት ቦታዎች በተጨማሪ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሱት ቦታዎች ተገኝተው መመልከት ይቻላል።
4. ተጫራቾች ከጨረታ ሠነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ብቻ ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስማቸውን፣ ክ/ከተማ፣ ወረዳ፣ የቤት ቁጥርና ስልክ ቁጥራቸውን እና ማንነታቸውን የሚገልጽ የፋዳ መታወቂያ በግልጽ በመፈረም ማቅረብ አለባቸው።
5. ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚመጡ የጨረታ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
6. ጨረታው ሐምሌ 08/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 5፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ይከፈታል።
7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው ከከፈሉ በኋላ ንብረቶቹን በ15 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
8. ለተሽከርካሪዎች የስም ማዞሪያ ወጭዎች እና ንብረቶቹን ለማንሳት የሚያስፈልግ ማንኛውም ወጭ ሙሉ በሙሉ በገዥዎች ይሸፈናል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- አድራሻ አዲስ አበባ ምድር ኃይል ግቢ መከላከያ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ስልክ ቁጥር 011 318-5163/ 011 318–5100 መደወል ይቻላል።
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር
Tender details
- Deadline: 2026-07-15
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-07-15 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Defense Minister Director General of General Service Finance Directorate
- Buyer address: አዲስ አበባ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የመከ/ዋና መስሪያ ቤት አዲሱ ህንፃ ብሎክ ሲ 4ኛ ፎቅ የግዥ ቡድን
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published: Jun 23, 2026
- Posted at: 2026-06-23T09:16:07.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.