በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው ልዩ ልዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 21/2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው አዳዲስ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ ፣ ኮስሞቲክስ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ፣ ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ እቃዎች)፣ ምግብ ነክ ፣ ኮንስትራክሽን እቃዎች (የቧንቧ እቃዎች)፤ ተሽከርካሪ መለዋወጫ (የመኪና ጎማዎች እና ቸርኬ) እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፣
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታከስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ : ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦከሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡
3. በግልፅ ጨረታ ላይ የወጡትን ሞተር ሳይክሎች ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ሳያስፈልገው በቀበሌ መታወቂያ ብቻ የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ፡፡
4. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል፡፡
5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና ጨረታው የሚያበቃበት ቀን እና ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ፦
|
ተ.ቁ |
የእቃው ኣይነት |
የጨረታው አይነት |
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመበት ቀን |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
ጨረታው የሚዘጋበት ሰዓት |
ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት |
ስልክ ቁጥር |
|
1. |
አዳዲስ አልባሳት |
ግልፅ |
15/10/2018 |
22/10/2018 |
4:00 |
4:30 |
022 111 8429/ 022 211 8925 |
|
2. |
ኤሌክትሮኒክስ |
ግልፅ |
15/10/2018 |
22/10/2018 |
4:00 |
4:30 |
022 111 8429/ 022 211 8925 |
|
3. |
ኮስሞቲክስ |
ግልፅ |
15/10/2018 |
22/10/2018 |
4:00 |
4:30 |
022 111 8429/ 022 211 8925 |
|
4. |
ተሽከርካሪ መለዋወጫ |
ግልፅ |
15/10/2018 |
22/10/2018 |
4:00 |
4:30 |
022 111 8429/ 022 211 8925 |
|
5. |
ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) |
ግልፅ |
15/10/2018 |
22/10/2018 |
4:00 |
4:30 |
022 111 8429/ 022 211 8925 |
|
6. |
ምግብ ነክ |
ግልፅ |
15/10/2018 |
22/10/2018 |
4:00 |
4:30 |
022 111 8429/ 022 211 8925 |
|
7. |
የኮንስትራክሽን እቃዎች (የቧንቧ |
ግልፅ |
15/10/2018 |
22/10/2018 |
4:00 |
4:30 |
022 111 8429/ 022 211 8925 |
|
8. |
ተሽከርካሪ መለዋወጫ (የመኪና ጎማ እና ቸርኬ |
ግልፅ |
15/10/2018 |
22/10/2018 |
4:00 |
4:30 |
022 111 8429/ 022 211 8925 |
|
9. |
ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች |
ግልፅ |
15/10/2018 |
22/10/2018 |
4:00 |
4:30 |
022 111 8429/ 022 211 8925 |
6. በግልፅ ጨረታ ሽያጭ ላይ የእቃዎቹ አስመጪ ወይም የአስመጪ ቤተሰብ መሳተፍ አይችሉም፡፡ ነገር ግን በጨረታዉ ተሳትፈዉ ቢገኙ በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ።
7. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ እቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) (Customs commission Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
8. በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ ስለሚገኙ ለግልፅ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስምንተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ጨረታው ይዘጋል።
9. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን ፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
11. ከላይ በተ/ቁ 10 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
12. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።
13. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።
የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት
በስልክ መስመር 09-05-11-5511 / 0116 668 828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ፡- አዳማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት
ስልክ ቁጥሮች 022 111 8429 እና 022 211 8925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-29
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-29 10:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Adama Custom Commission Branch Office
- Bid bond: 5% ለእያንዳንዱ ምድብ እቃዎች
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Jun 22, 2026
- Posted at: 2026-06-23T09:40:51.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.