የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የዱቄት ሳሙና እና የፈሳሽ ሳሙና በቋሚነት ሊያቀርቡ የሚችሉ አምራች ድርጅቶችን ብቻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:-SSNT-T623

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የዱቄት ሳሙና እና የፈሳሽ ሳሙና በቋሚነት ሊያቀርቡ የሚችሉ አምራች ድርጅቶችን ብቻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በዘርፉ (የዱቄት ሳሙና ወይም የፈሳሽ ሳሙና) በማምረት ሁለት (2) ዓመት እና ከዛ በላይ የሰሩ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በዘርፉ ከኢትዮጵያ የጥራትና ደረጃዎች ማረጋገጫ ባለስልጣን የጥራት ማረጋገጫ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣ ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የተሰጠ የአምራችነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የተፈላጊውን ምርት ናሙና ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ150 ቀናት የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንከ ዋስትና ማቅረብ አለበት። ከኢንሹራንስ እና ቅደመ ሁኔታ ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 14 ቀን 2018፣ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር (አንድ መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T623 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።

ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒውን እና የመወዳደሪያ ፋይናንሽያል ፕሮፖዛል ዋናውን እና ኮፒውን ፣ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን በተለያየ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ በሚገኘው ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል ሐምሌ 14 ቀን፣ 2018 ዓ.ም. እስከ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መከፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-517-4028/8025

ኢ-ሜይል: AynalemAy@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Tender details

  • Deadline: 2026-07-21
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid opening: 2026-07-21 15:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Buyer TIN: 0000028498
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jun 22, 2026
  • Posted at: 2026-06-23T09:45:13.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders