በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ የገነት ሆቴል የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የሰራተኞች ደንብ
ልብስ የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ኢንቨስትም ሆልድንግ ከሚተዳደሩት የመንግስት የልማት ድረጅት ውስጥ ገነት ሆቴል አስተዳደር ለሆቴል የሰራተኞች የደንብ ልብስ እና የሰራተኛ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን ቅድመ ሆኔታዎች የምታሟሉ ተጫራጮች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

  • የ2018 ዓ.ም ዘመን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት (VAT) ያላቸው፤ 
  • የግብር ከፋይ ምዝገባና ሰርተፍኬት መለያ ቁጥር (TIN ሰነድያላቸው)
  • በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት ፤
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ሀያ ሺህ ብር (20,000) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ “ለገነት ሆቴል” በሚል በማሰራት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  • ተጫራጮች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ታሳቢ የሚደርግ በአስራ አምስት (15) ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ ከድርጅታችን የፋይናንስ ቢሮ ክፍል ሰነዱን የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) ለያንዳነዱ የጨረታ ሰነድ ከፍለው መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
  • ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት አለት ጀምሮ ባሉ አስራአምስት (15) ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ ይሆናል።
  • መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ጨምሮ የሚያቀርቡበትን ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት(15) ቀናት ውስጥ ለገነት ሆቴል አስተዳድር ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል በአሰራ አምስተኛው ቀን አሰከ 8፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የፋይናንስ ክፍል ቢሮ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል በአስራ አምስተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ የጨረታው መክፈቻ በቀጣይ ባለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
  • ጨረታው ተጫራጮች ተወካዮች ባሉበት በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 በድርጅቱ አዳራሽ ይከፈታል።
  • አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።
  • ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በ0939500000 0911999072
በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ የገነት ሆቴል


Tender details

  • Deadline: 2026-07-07
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት(15) ቀናት 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-07 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት(15) ቀናት 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Genet Hotel Administration
  • Buyer address: አ/አ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ላይ ገነት ሆቴል ግቢ ውስጥ
  • Bid bond: 20,000 (ሀያ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published: Jun 23, 2026
  • Posted at: 2026-06-23T11:41:47.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders