ዋሊፍ ኤዱኬሽን አክሲዮን ማህበር (Waliif Education S.C.) የ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 በጀት ዓመታት የሂሳብ መዛግብቱን በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ስታንዳርድ (IFRS) መሠረት የውጭ ኦዲት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ዋሊፍ ኤዱኬሽን አክሲዮን ማህበር (Waliif Education S.C.) የጨረታ ቁጥር፡ WE/AV/01/2018(ለአሴት ቫሉዌሽን) እና WE/EA/02/2018 (ለውጭ ኦዲት)

  • ጨረታዉ የወጣበት ቀን፡ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ዋሊፍ ኤዱኬሽን አክሲዮን ማህበር ለ2018 በጀት ዓመት የድርጅቱን የንብረትና የሀብት ግምት (Asset Valuation) ሥራ እና የ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 በጀት ዓመታት የሂሳብ መዛግብቱን በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ስታንዳርድ (IFRS) መሠረት የውጭ ኦዲት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ የጋራ መሠረታዊ መስፈርቶች (Eligibility Criteria) በየትኛውም ዘርፍ መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን ህጋዊና ሙያዊ ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፦

  • በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
  • የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡ መሆናቸውን የሚያሳይ የግብር ማረጋገጫ (Ja× Clearance Certificate)።
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (0)።
  • ተጫራቾች የቴክኒክ (Technical Proposal) እና የፋይናንስ (Financial Proposal) ሰነዶቻቸውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ (Original እና Copy በማለት) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለእያንዳንዱ ዘርፍ ብር 10,000 (አሥር ሺህ ብር) በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም የማይሸረፍ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከቴክኒክ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

2. የየዘርፎቹ ልዩ የሥራ ዝርዝር እና ልዩ መስፈርቶች

ክፍል 1፦ የንብረትና የሀብት ግምት (Asset Valuation) ሥራ

የሥራው ዝርዝር (Scope of Work)፦ የአክሲዮን ማህበሩን ዋና መሥሪያ ቤት ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች (ለገጣፎ፣ ቢሾፍቱ፣ ገላን ጉዳ፣ አምቦ፣ ነቀምቴ (3 ት/ቤቶች)፣ በደሌ፣ ቡል ሆራ፣ ሻኪሶ፣ ጂማ፣ እና ባሌ) የሚገኙ 12 ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ይዞታዎች፣ ንብረቶችና ኢንቨስትመንቶች በ IFRS እና IVS መሠረት ሦስቱን ዋና ዋና የሀብት ክፍሎች (ቋሚ፣ የማይጨበጡ እና የፋይናንስ ኢንቨስትመንቶች) መገመት።

ልዩ የሙያ መስፈርት፦

  • በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ (AABE) የተሰጠ እና በዘመኑ የታደሰ የአሴት ቫሉዌሽን ሥራ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት።
  • የአክሲዮን ማህበራትን ወይም ተመሳሳይ ግዙፍ ተቋማትን የሶስቱንም የአሴት አይነቶች በጋራ (Combined) የመሥራት ቢያንስ የ3 (ሦስት) ዓመት እና ከዚያ በላይ የተረጋገጠ የሥራ ልምድ ማስረጃ።
  • ዋና ባለሙያዎች (Key Personnel) በAAB የተመዘገቡ፣ በEBS እና IS ዙሪያ በቂ እውቀት ያላቸው መሆን አለባቸው።

 ክፍል 2፦ የውጭ ኦዲት አገልግሎት ሥራ

  • የሥራው ዝርዝር (Scope of Work)፦ የማህበሩን የ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 በጀት ዓመታት የሂሳብ መዛግብት በ IFRS መሠረት ኦዲት ማድረግ፡ የፋይናንስ አሸናፊው የአራቱን ዓመታት (2015፣ 2016፤ 2017 እና 2018) የኦዲት ሪፖርት በተስማማው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለይቶ ማጠናቀቅ አለበት።

ልዩ የሙያ መስፈርት፦

  • የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ወይም በAABE የተሰጠ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ።
  • በ AABE ዘንድ በ”Public Interest Entity (PlE)” ደረጃ የተመዘገቡ ወይም የአክሲዮን ማህበራትን ሂሳብ በ IFRS ለመመርመር ሙሉ ፍቃድ ያላቸው መሆን።
  • የአክሲዮን ማህበራትን የ IFRS የውጭ ኦዲት ሥራዎችን በተሳካ ሁኔታ ያከናወነበትና ቢያንስ የ 5 (አምስት) ዓመት አጠቃላይ የኦዲት ልምድ።
    ለሥራው የሚሰማራው ቡድን በ IFRS ላይ በቂ እውቀትና ዓለም አቀፍ የሙያ ማረጋገጫ (እንደ ACCA, CPA ያሉ) ያላቸው መሆን እና ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳ (Timeframe) ማቅረብ።

3. የጨረታ ሰነድ መግዣ፣ መዝጊያና መክፈቻ ጊዜያት

  • የሰነድ መግዣ፦ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዋናው መሥሪያ ቤት የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይቻላል።
  • የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ሰዓት፦ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ፣ በዚያኑ ዕለት ከቀኑ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • (ማሳሰቢያ፡ ዕለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል)።
  • ማሳሰቢያ፦ ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ እና ስልክ ቁጥር
ዋሊፍ ኤዱኬሽን አክሲዮን ማህበር ዋና መሥሪያ ቤት
አዲስ አበባ ከተማ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 9፣ አዋሽ ባንክ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 302
ስልክ ቁጥር፦ +251 96 130 0180 / +251-91 307 8297 / +251-10 117 426 ኢሜይል፦ nwesc25@gmail.com 


Tender details

  • Deadline: 2026-07-03
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-03 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ዋሊፍ ኤዱኬሽን አክሲዮን ማህበር (Waliif Education S.C.)
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ ዘርፍ ብር 10,000 (አሥር ሺህ ብር)
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 24, 2026
  • Posted at: 2026-06-24T08:59:56.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders