ዘኔቸር ኤንድ ባዮዳይቨርሲቲ ኮንሰርቬሽን ዩኒዬን ኢትዮጵያ (The Nature and Biodiversity Conservation Union Ethiopia) 860 ኬንያ ቶፕ ባር የተሰኘ የንብ ቀፎ ከህጋዊ አምራቾች አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የንብ ቀፎ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

ዘኔቸር ኤንድ ባዮዳይቨርሲቲ ኮንሰርቬሽን ዩኒዬን ኢትዮጵያ (The Nature and Biodiversity Conservation Union Ethiopia) የደቡብ ምዕራብ ክልል ጽ/ቤት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ እና በቤንች ሽኮ ዞንኖች በሚገኙ ወረዳዎች እየተገበረ ላላቸዉ Forest Connect እና Wetland Management ፕሮጀክቶች ለሚደገፉ ተጠቃሚዎች የሚሰራጭ 860 ኬንያ ቶፕ ባር የተሰኘ የንብ ቀፎ ከህጋዊ አምራቾች አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ከታች የተቀመጠውን ዝርዝር መስፈርት የምታሟሉ ህጋዊ አምራቾች አቅራቢዎች የምርት መግለጫ (Product Specification) ላይ በተቀመጠዉ መሰረት ቫትን ጨምሮ የአንዱን ቀፎ መሸጫ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ (Proforma) ሞልታችሁና በኤንቬሎፕ አሽጋችሁ ቦንጋ ከተማ ብሔራዊ ቡና ሙዚዬም ከፍ ብሎ በሚገኘው የናቡ ኢትዮጵያ ደ/ም/ኢ/ጽ/ቤት ወይንም ቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን-አማን ከተማ አቶ ሰይድ ህንጻ ላይ በሚገኘው የድርጅታችን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከቀን 17/10/2018ዓ.ም እስከ 23/10/2018 ዓ.ም በሥራ ሰዓት ዉስጥ እንድታስገቡ እያሳሰብን ጨረታዉ በቀን 26/10/2018ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በቦንጋ ከተማ በሚገኘው የናቡ ኢትዮጵያ ደ/ም/ኢ/ጽ/ቤት የሚከፈት መሆኑንን እንገልጻለን።

በጨረታውን ለመወዳደር መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

1. የ2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለዉ፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈለ፣

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆነ፣

4. ሎሚከፈለው ገንዘን ሕጋዊ ደረሰኝ መስጠት የሚችል

5. ከላይ የተጠቀሱትን ህጋዊ ሰነዶች ኮፒ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፣

ማሳሰቢያ፡

የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ከሰኔ 18-23/2018 ዓ.ም ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል ?

  • ተጫራቾች ከላይ በቁጥር የተጠቀሰዉን የቀፎ መጠን ሰረተዉ ለተቋሙ የሚያስረክቡበትን ጊዜ በጨረታዉ ዋጋ ማስገቢያ ሰነድ ዉስጥ መግለጽ አለባቸዉ።
  • ከዚህ ቀደም ለተለያዩ ተቋማት ጥራቱን የጠበቀ የንብ ቀፎ ውል በገባበት ጊዜ ውስጥ በማስረከብ የእውቅና ሰርተፍኬት ያለው አቅራቢ ሰርተፍኬቱን ማያያዝ ይጠበቅበታል።
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የሚገዛው የኬኒያ ቶፕ ባር ቀፎ ዝርዝር የምርት መግለጫ (Product Specification)

ሀ. እያንዳንዱ የንብ ቀፎ የሚሰራው ከበሰለና በደንብ ደርቆ ከወጣስት የዋንዛ እንጨት ይሆናል።

በተጨማሪም፦

1. ቀፎው የሚሰራበት ጣውላ በምንም ዓይነት ተሕዋስያን፣ ተባይና ነፍሳት ያልተጠቃ መሆን አለበት፣

2. ጣውላው ያልተሰነጣጠቀ፣ ቋር የሌለበትና ምንም ዓይነት ቀዳዳ የማይታይበት መሆን ይኖርበታል።

ለ. የሚሰራው የኬንያ ቶፕ ባር የንብ ቀፎ ዲዛይንና መጠን የተለያዩ ክፍሎች እንደሚከተለው ነው።

የቀፎው መጠን

1. ርዝመት 1 ሜትር

2. የላይኛው ጎን ስፋት 40 ሳ.ሜ

3. የታችኛው ጎን ስፋት 22 ሳ.ሜ

4. ከፍታ 30 ሳ.ሜ

5. የቀፎ ክዳን (Roof) ስፋቱ 60 ሳ.ሜ፣ ርዝመቱ 120 ሳ.ሜ ሆኖ ውፍረቱ 2 ሳ.ሜ በሆነ ጣውላ የሚሰራ ሲሆን በልሙጥ ፐርሊን ቆርቆሮ መሸፈን አለበት።

የቀፎው ዲዛይን

ከታች በምስሉ ላይ እንደተመለከተው ሲሆን የጎን ግድግዳዎች ወይም ጣውላዎችና መወጠሪያዎች በምስሉ መሰረት ርቀታቸው ጠብቀው የሚሰሩ ይሆናል። በአንደኛው የቀፎው ፊት የታችኛው ክፍል የንቦች መግቢያ በር ይኖረዋል።

ምስሉን ከ ጨረታው ጋር በተያያዘው ዶክመንት ላይ ያገኙታል 

ሐ. የቀፎ ርብራቦች (Frames) ለአንድ ቀፎ በድምሩ 30 ሲሆኑ እያንዳንዱ ርብራብ (Frame) ስፋቱ 3.2 ሴንቲ ሜትር፣ ውፍረቱ 2 ሴንቲ ሜትር ሆኖ መሃሉ ለስም መቀቢያ የሚሆን መስመር (Wax starter strip) ሊኖረው ይገባል:: ተጨማሪ ማብራሪያዎች በባለሙያ የሚሰጡ ይሆናል::

መ. ኬንያ ቶፕ ባር የንብ ቀፎ ተገጣጥሞ ሲታይ ከታች በምስሉ እንደሚመለከተው ሆኖ አራቱም የጎን ግድግዳዎች ከውጭ በኩል ቢጫ ቀለም መቀባት አለባቸው። እንደዚሁም በአንዱ በኩል ባለው የግድግዳው ፊት መሃል ላይ የንቦች መውጫና መግቢ በር ኖሮት ለንቦች መወጣጫ የሚሆን አነስተኛ ጣውላ በምስሉ ላይ በሚታየው መሰረት መኖር አለበት።

ምስሉን ከ ጨረታው ጋር በተያያዘው ዶክመንት ላይ ያገኙታል 

Head Office Addis

Sisay Asfaw

Executive Director

Mobile +251 (0) 911 57 49 03

Sisay.Asfaw.nabu@gmail.com

Ref: NABU/FC-046/2026

Addis Ababa, 23 June 2026

The Nature and Biodiversity Conservation Union Ethiopia (NABU Ethiopia)

Head Office Addis Ababa

Wubget Building

Urael Street. P.O. Box: 62483.

Kirkos Sub-city Woreda 17/18

Addis Ababa, Ethiopia

Tel. +251 (0) 11 552 37 44

+251 (0) 11 552 36 41

Fax +251 (0) 11 552 37 60

NABU international office in Ethiopia is converted to NABU Ethiopia as a local CSO in January 2023.

Following the conversion, NABU Ethiopia is registered and licensed in Ethiopia as a local Civil Society Organization by the Civil Society Organization Authority in accordance with the Proclamation No. 1113/2019.

Registration number: 1922

NABU Ethiopia is an affiliated organization to

NABU international.

NABU Headquarters

Charitéstraße 3, 10117 Berlin, Germany

Tel. +49 (0)30 28 49 840

Fax +49 (0)30 28 49 84 20 00

NABU@NABU.de: www.en.NABU.de

NABU counts on more than 100 years of experience in conservation works in Germany and is active in Ethiopia since 2006. Our work connects ecologic and social aspects and ranges from climate change adaptation to environmental education and from support for protected areas such as biosphere reserves to sustainable income generating activities.


Tender details

  • Deadline: 2026-06-30
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-07-03 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Nature and Biodiversity Conservation Union (NABU)
  • Published: Jun 24, 2026
  • Posted at: 2026-06-24T09:06:56.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders