የአማራ ሴቶች ማህበር የንጽህና መጠበቂያ እንዲሁም ሌሎች ግብአቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

አማራ ሴቶች ማህበር

Amhara women Association

ቁጥር/Ref:- አሴማ/08/ 131 /ስ/ለ-5

የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ

የጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ሴቶች ማህበር በሲቪል ማህበረሰብ አዋጅ ቁጥር 194/2004 አንቀጽ 63 (1) መሰረት የአማራ ሴቶች ማህበር የኢትዮጲያ ማህበር ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን የመዝገብ ቁጥር 016 ነው። የአማራ ሴቶች ማህበር በሁሉም የአማራ ክልል ዞን፣ ወረዳ እና ቀበሌ የተለያዩ የልማት ስራዎች የሚያከናውን ዘርፈ ብዙ የልማት ድርጅት ነው። ድርጅታችን በአሁኑ ሰዓት ከ6 ፕሮጀክቶች በላይ በሁሉም ዞኖች፣ ወረዳ እና ቀበሌዎች በመተግበር ላይ ይገኛል። በዚሁም መሠረት ድርጅቱ በሥሩ ለሚገኝ ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች የንጽህና መጠበቂያ ግብአቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከታች የተዘረዘሩትን እቃወች ማቅረብ የሚችሉ ህጋዊ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

.

የእቃዉ አይነት

መለኪያ

ጠቅላላ ብዛት

1

ሳሙና የልብስ (250.) እንዲሁም የገላ ሳሙና 180 . ለንጽህና መጠበቂያ አገልግሎት የሚውል

በቁጥር

2077

2

የሴቶች ፓንት ሁለት በአንድ (2 piece in one)

በቁጥር

2077

3

የክብር ንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ) እንደገና ታጥቦ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል

ጥቅል/3/

በአንድ

2077

4

የእጅ ባትሪ ( ቻርጅ የሚደረግ እና በሶላር የሚሰራ)

በቁጥር

2077

5

ፒጃማ ()

ጥር

2077

6

የጨርቅ ቦርሳ፣ (ሳሙና 250. የውስጥ ልብስ(ፓንት)እና ሞዴስ (የንጽህና መጠበቂያ) የእጅ ባትሪ ሊይዝ የሚችል

በቁጥር

2077

  1. ተወዳዳሪዎች በዘርፋ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ አና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነበር/ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ /ክሊራንስ/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች እነዚህን እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃወች ኮፒ በማድረግ በጀርባው ፊርማና ማህተም በማድረግ በማጫረቻ ሰነዳቸው ለይ ማካተት ይኖርባቸዋል።
  2. ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ዓየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ሰኔ 25/2018 ከስአት 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጨረታዉ ባህር ዳር ባለው ዋና መ/ቤት ይከፈታል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከቀረበው ጠቅላላ ዋጋ 2% ሲፒኦ በድርጅቱ ስም በማሰራት ከጨረታ ዶክመንቱ ጋር በማያያዝ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫተቾች የእቃዎቹን ናሙና ማቅርበ ይጠብቅባችዋል ያላቀረበ ተጫራች ውድቅ መሆኑን እንገልጻለን።
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ማለትም የዋጋ ሰነዳቸውን በታሸገ ፓስታ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ተወዳዳሪዎች የፋይናንስ እና የቴክኒክ መስፈርቶችን በተለያዩ ፋይሎች በተዘጋጀ ሁኔታ ማቅረብ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡበት ጊዜ /delivery time/ ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በ5 /አምስት/ ተከታይ ቀናት ውስጥ ብቻ ይሆናል።
  8. ተጫራቾች ሰነዱን ባህር ዳር በሚገኘው አማራ ሴቶች ማህበር ዋናው መ/ቤታችን ቀበሌ 13 ፖሊስ ኮሚሽን ፊትለፊት በጋዜጣዉ ላይ በተጠቀሱት ቀናት መሰረት ከጠዋት 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰአት በኋላ 7፡00 ሰዓት አሰከ 10፡00 ሰአት የሚያገኙ ይሆናል። የጨረታ ሰነዱን ባህር ዳር በሚገኘው ዋና መ/ቤት ከፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
  9.  ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ለበለጠ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር 09 42 83 58 40/ 09 18 78 01 55


Tender details

  • Deadline: 2026-06-29
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-07-02 14:30
  • Bid opening (note): ሰኔ 25/2018 ከሰአት 8፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara women Association
  • Bid bond: 2%
  • Published: Jun 24, 2026
  • Posted at: 2026-06-24T10:32:41.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders