ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኃ.የተ.ግ.ማህበር (ኖክ) ቃሊቲ መጋዘን ውስጥ ያሉትን ባለ 1ኛ ደረጃ ፓሌቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ጉዳዩ፡- ጨረታን ይመለከታል፡፡
ኩባንያችን ቃሊቲ መጋዘን ውስጥ ያሉትን ባለ 1ኛ ደረጃ ፓሌቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ የእቃው ዝርዝር እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
|
ተ.ቁ |
የፓሌት / የሞራሌ ዓይነት |
ብዛት |
|
1 |
1ኛ ደረጃ ፓሌት |
2,000 |
ስለሆነም ድርጅታችን ፓሌቶቹን ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች ፓሌቶቹን እንደከዚህ ቀደም መምረጥ እንደማይችሉ ከወዲሁ ማሳሰብ ይወዳል፡፡ ከላይ ለተጠቀሰው እቃ ዋጋ በመስጠት መወዳደር ይቻላል፡፡ እቃውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅዳሜ እና እሁድን ሳይጨምር ቦታው ላይ በመመልከት የሚገዙበትን ዋጋ ከ15 በመቶ ቫት ጋር በመግለጽ ድርጅቱ ለዚህ ጨረታ ያዘጋጀውን ፎርም በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው ሊሆን ይገባል፡፡ እንዲሁም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ቢድ ቦንድ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ በማቅረብ መጫረት ይቻላል፡፡
አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ በተገለጸለት በሦስት የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን በአንድ ጊዜ ክፍያ መፈጸም ይኖርበታል፡፡ ይህንን ባይፈጽም ለጨረታው ያስያዘውን ገንዘብ በሙሉ የማይመለስ በመሆኑ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡ አሸናፊ እቃውን በአስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት (ቅዳሜ እና እሁድን ሳይጨምር) ከቃሊቲ መጋዘን ማንሳት አለበት፡፡ ይህ ባይሆን የመጋዘን ኪራይ በቀን 3,000.00 ብር ይከፍላል፡፡ ሙሉ ክፍያ ሲፈጽም ብቻ ሲፒኦው ተመላሽ ይሆናል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁ. 011-618-7165 ወይም 011-439-0378 መደወል ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- ቦሌ ኤርፖርት መንገድ ከፍሬንድሺፕ ህንፃ ፊት ለፊት ያለው የኖክ ዋ/መስሪያ ቤት
ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኃ.የተ.ግ.ማህበር (ኖክ)
Tender details
- Deadline: 2026-06-30
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅዳሜ እና እሁድን ሳይጨምር
- Bid opening: 2026-06-30 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: National Oil Ethiopia PLC
- Buyer TIN: 0000059459
- Buyer address: ቦሌ ኤርፖርት መንገድ ከፍሬንድሺፕ ህንፃ ፊት ለፊት ያለው የኖክ ዋና መስሪያ ቤት
- Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
- Published: Jun 24, 2026
- Posted at: 2026-06-24T11:46:04.000Z
- Buyer website: https://www.nocethiopia.com/
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.