የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ተሽከርካሪዎች በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች ከቀን 19/10/2018 ዓ.ም ጀምሮ በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች:

  1. የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
  2. ለሀራጅ ጨረታው ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ 200,000 ብር (ሁለት መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማስያዝ የሚችል፤
  3. ተጫራቹ ለሀራጅ ጨረታ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱያቀርባል፤
  4. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ተሽከርካሪ ወዲያውኑ ከፍሎ በዐ5 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፤
  5. ተሽከርካሪ አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በዐ5 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
  6. በጨረታው ያላሸነፋ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
  7. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
  8. ማንኛውም ተጫራች ተሽከርካሪውን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤
  9. ተጫራቹ ተሽከርካሪውን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፤
  10. የሀራጅ ጨረታው የሚካሄደው በቀን 23/10/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤

N.B፦

  • አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ መኪናውን ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።
  • የሻንሲ እና የሞተር ቁጥር የተመታ ተሽከርካሪ ገዝተው መንገድ ትራንስፖርት ሰሌዳ ቁጥር ሲያወጡ መሸጥ እና መለወጥ የማይችሉ እና ቀይ ምልክት ያለው ሰሌዳ በመስጠት በመንገድ ትራንስፖርት በኩል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-30
  • Publishing entity: Ethiopian Revenue and Custom Commission Jigjiga Branch Bureau
  • Bid bond: 200,000 ብር እያንዳንዱ ተሽከርካሪ
  • Published: Jun 25, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders