የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት እቃ ኮንስትራክሽን፣ አልባሳት፣ እስፔርፓርት፣ የፅዳት ዕቃ፣ ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሀራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የግልፅ እና የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት እቃ ኮንስትራክሽን፣ አልባሳት፣ እስፔርፓርት፣ የፅዳት ዕቃ፣ ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሀራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች 23/10/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
2. ለሀራጅ ጨረታው 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ (C.RO) ማቅረብ የሚችል፤
3. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
4. ለሀራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል፤
5. ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
6. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን እቃ ክፍያውን በ05 ቀናት ውስጥ መፈፀም አለበት፤
7. እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.RO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
8. በጨረታው ያላሸነፈ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
9. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
10. ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤
11. ተጫራቹ እቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፤
12. ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ከቀን 23/10/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የእቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ25/10/2018 ዓ.ም 3:45 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤
13. የሀራጅ ጨረታው የሚካሄደው በ25/0/2018 ከጠዋቱ 4፡15 በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤
N.B: አሸናፊ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-02
- Publishing entity: Ethiopian Revenue and Custom Commission Jigjiga Branch Bureau
- Published: Jun 25, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.