በቂሊንጦ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል ለህብረት ሱቅ እና መዝናኛ ክበባት አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በቂሊንጦ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል ለህብረት ሱቅ እና መዝናኛ ክበባት አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን ማለትም የተፈጨ ቡና፣ የለውዝ ቅቤ፣ የሻይ ቅጠል፣ የዳቦ ዱቄት፣ የዳቦ እርሾ፣ የዳቦ ማኮፈሻ፣ ጨው፣ የምግብ ዘይት፣ የወጥ ማጣፈጫ ቅመም፣ ፕላስቲክ እሽግ ጁስ ባለ፣ ፕላስቲክ እሽግ ማር፣ እሽግ ውሃ፣ ኢንዶሚን፣ ወተት፣ እርጎ፣ ዱቄት ወተት፣ ገብስ ቆሎ፣ ማርማራታ፣ ማርጋሪን፣ የአሳ ሰርዲን የዶሮ ዕንቁላል፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ አፕል፣ ሙዝ፣ ማንጎ፣ አቮካዶ፣ ብርትኳን፣ ፓስታ፣ ማካሮኒ፣ አተር፣ ባቄላ፣ ምስር፣ ሩዝ፣ ዛላ በርበሬ፣ ቸኮሌት፣ ከረሜላ፣ ማስቲካ የገላ ሳሙና፣ የልብስ ሳሙና፣ ፈሳሽ ሳሙና፣ አይጃክስ፣ የዱቄት ሳሙና፣ የፀጉር ቅባት፣ የፊት ክሬሞች፡ ሎሽን፣ ቫዝሊን፣ ሻምፖ፣ ዶድራንት፣ የጥርስ ብሩሽ የጥርስ ሳሙና፣ የፂም መላጫ፣ የጥፍር መቁረጫ፣ ነጠላ ጫማ፣ ደብተር፣ እስክሪቢቶ፣ ልሙጥ ወረቀት፣ የሻይ ማሽን፣ የወንዶች የፀጉር ማሸን፣ የማቀዝቀዣ ፍሪጅ እና የመሳሰሉትን ሸቀጣ ሸቀጦች አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል።

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መመሪያና መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1, በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን፣ በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለፀ መሆን አለበት።

2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ።

3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።

4. የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል አቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን የዘመኑን ግብር ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

5 ከደረጃ መዳቢዎች የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

6. ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።

7.የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 150.00/አንድ መቶ ሃምሳ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል ስም በአካውንት ቁጥር 1000029497498 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ስራ ከፍል ቢሮ ቁጥር 21 መግዛት ይችላሉ።

8. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት።

9. ቴክኒካልና ፋይናንሽል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳደሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል።

10. ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገቡት ሰነድ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ቁጥር በትክከል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ሰነድ፤ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም።

11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲ ፒ ኦ ከቴክኒካል ሰነዶች ከኦርጅናሉ ጋር በአንድ ለይ አሸገው ማቅረብ አለባቸው።

12, ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000/ሃያ አምስት ሺህ ብር / በባንክ በተረጋገጠ CPO በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ስም አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሽገ ፖስታ እስከ ሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 21 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው እንዲሁም የባንክ ዋስትና የሚያስይዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆኑ ይኖርበታል።

13. ጨረታው ሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ቂሊንጦ በሚገኘው በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።

14.ሆኖም ጨረታው! ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ ጨረታው አይስተጓጎልም ወይም ውድቅ አይሆንም።

15. የጨረታው ዝርዝር መመሪያ በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝሮ ቀርቧል።

16. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም እንዲሁም ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

17. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

18. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የአመት በዓላት ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ጨረታው ይከፈታል።

አድራሻ፡- ቂሊንጦ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል አ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0114 522 778 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

ቂሊንጦ

የቂሊንጦ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል


Tender details

  • Deadline: 2026-07-03
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-07-03 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Correctional Facility Kilinto
  • Bid bond: 25,000.00 ብር
  • Bid document price: 150.00 ብር
  • Published: Jun 26, 2026
  • Posted at: 2026-06-26T08:00:41.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders