በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ያገለገሉ ማሽኖች፣ ፕላስቲኮች፣ የብረት ቀለም /431/ እና ያገለገሉ የመኪና ዕቃዎች ሽያጭ፣ የውጭ ኦዲት አገልግሎት ግዥ፣ ደንደዓ የዳቦ ስንዴ ሽያጭ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥና መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥና መግዛት ይፈልጋል፤

  • ሎት አንድ፡ የተለያዩ ያገለገሉ ማሽኖች፣ ፕላስቲኮች፣ የብረት ቀለም /431/ እና ያገለገሉ የመኪና ዕቃዎች ሽያጭ
  • ሎት ሁለት- የውጭ ኦዲት አገልግሎት ግዥ
  • ሎት ሶስት፡- ደንደዓ የዳቦ ስንዴ ሽያጭ

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ -

1. ተጫራቾች ለሎት አንድ ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ መጫረት የሚችል ሲሆን ለሎት ሁለት በዘርፉ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት አንድ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፣ ለሎት ሁለት ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)፣ ለሎት ሦስት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ብቻ በማሰራት ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት እስከ ቀኑ አስር ሠዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ ዋናና ቅጅ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኢንተርፕራይዙ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኙበት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 በግልፅ ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ወይም በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓትና ቦታ በግልፅ ይከፈታል። /ትክክለኛው የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል።

6. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።

7. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን/+251 92 575 0633 / 09 13 49 72 04 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-10
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-07-10 12:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Debre Birhan University
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jun 26, 2026
  • Posted at: 2026-06-26T08:08:12.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders