ታህሰብ የንግድ ሥራዎች አክሲዮን ማህበር ያገለገሉ ብዛት ያላቸው በሮች፣ መስኮቶች እና ሌሎች የተለያዩ ብረታ ብረቶች እና መስታወቶች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ታህሰብ የንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበሩ ያገለገሉ ብዛት ያላቸው በሮች፤ መስኮቶች እና ሌሎች የተለያዩ ብረታ ብረቶች እና መስታወቶች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
1. የዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ( ቲን ) ቁጥር ያለው፤
3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ( አስራ አምስት ) ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከቀኑ 3፡00 አስከ 10፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ እስከ 5፡30 ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል ብሎክ 8 አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸ በተገኙበት በአክሲዮን ማህበሩ ጽ/ ቤት ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል።
5. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ በማድረግ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
6. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ዋስትና ) በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ ) ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺ ብር ) በአክሲዮን ማህበሩ ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር መመለስ ይኖርበታል።
8. የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ( ግለሰብ ) በውስጥ ማስታወቂ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በራሱ ወጪ ማንሳት ይኖርበታል።
9. አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማስረጃ ስልክ ቁጥር 011 279-3065
ታህሰብ የንግድ ሥራዎች አክሲዮን
ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-07-10
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከቀኑ 3፡00 አስከ 10፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ እስከ 5፡30 ድረስ
- Bid opening: 2026-07-10 16:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tahseb Business S.C.
- Bid bond: 15,000.00 (አስራ አምስት ሺ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ) ብር
- Published: Jun 26, 2026
- Posted at: 2026-06-26T08:08:24.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.