Pipes, valves and fittings

በማእከላዊ ኢትዮጵያ በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡታጅራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት አሮካሪያ እና ሳይፕረስ ችግኝ፣ የውሃ ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች እንዲሁም የግንባታ እቃዎች (የአርማታ ብረትና ሲሚንቶ) በሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

በማእከላዊ ኢትዮጵያ በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡታጅራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለ2018 በጀት ዓመት ውል ገብቶ ለሚሰራቸው ፕሮጀክቶች ስራ አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት-1 አሮካሪያ እና ሳይፕረስ ችግኝ
  • ሎት-2 የውሃ ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች
  • ሎት-3 የግንባታ እቃዎች (የአርማታ ብረትና ሲሚንቶ) በሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም፡- ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶችና ማስታወቂያው ማሟላት አለበት፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ በፋይናንስ ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና ተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ከፋይ ለመሆናቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃዎችን ከዋናው ጋር የተገናዘበ በፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።

2. ዕቃዎቹም የጨረታ ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ቡታጅራ ከተማ ውሃ አቅርቦትና ፍሣሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500(አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ የሚቻል ሲሆን አድራሻችንም ከቡታጅራ ከተማ ንግድ ባንክ በስተጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጎን ይገኛል።

3. የሚጫረቱባቸው ሎት በመለየት በዓይነታቸው የሚሸጡባቸውን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የሚጫረቱባቸውን ዘርፍና የተጫራቹን ስም በግልፅ በመፃፍ የድርጅቱ ማህተም አርፎበት በአስራ ስድስተኛው ቀን ሰነዱን በገዙበት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በነዚሁ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ጨረታው ከቀኑ 8፡00 በ16ኛው ቀን የጨረታው ሳጥኑ ታሽጐ ከቀኑ 8፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት መስሪያ ቤቱ ተጫራቾች ወኪሎቻቸው ባይኖሩም ጨረታው ከመክፈት አይታገድም።

5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስተና ለእያንዳንዱ ሎት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. በጨረታ የተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

7. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል በገባበት ቀን ካላቀረበ ለጨረታ ማስመስከሪያ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስም።

8. ማንኛውም ተጫራች ሌላው ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም።

9. አሸናፊ ድርጅቶች ማሸነፋቸው እንደተገለፀላቸው ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መግባት ይኖርባቸዋል።

10. አሸናፊው ድርጅት እቃዎችን መ/ቤቱ ድረስ አምጥቶ የሚያስረክብ መሆኑን እንገልፃለን። 

11. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ሊገኙ ባይችሉ መ/ቤቱ ጨረታውን ከፍቶ የሚያወዳድር መሆኑን እንገልፃለን።

12. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፡-
Fax 251-46 115 1793/ Mobile 09 10 96 68 23/ 09 20 89 46 22
P.O. Box 16
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡታጅራ ከተማ ውሃ
አቅርቦትና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-13
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00
  • Bid opening: 2026-07-13 14:30
  • Bid opening (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Butajira Water Works Construction Enterprise
  • Bid bond: 100,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jun 27, 2026)
  • Posted at: 2026-06-27T07:10:05.000Z
← Back to all tenders