Pipes, valves and fittings

ሚድሮክ ጂኦ ኤክስፕሎሬሽን አገልግሎት ኃ.የተ.የግ.ማ የተለያዩ አይነት እና መጠን ያላቸው የውሃ ቧንቧ (ፓይፕ) እና ፊቲንግ እና ሌሎች እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

IMMIGROUP

MIDROC GEO EXPLORATION SERVICE PLC

ሚድሮክጂኦሼክስኘሎሬሽንአገልግሎት ኃ/የተ/የግል ማህበር

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ

የጨረታ ማስታወቂያ

Document No. MGEO/OF/GM/001

ሚድሮክ ጂኦ ኤክስፕሎሬሽን አገልግሎት ኃ.የተ.የግ.ማ ከዚህ በታች የተገለፁት የተለያዩ አይነት እና መጠን ያላቸው የውሃ ቧንቧ (ፓይፕ) እና ፊቲንግ እና ሌሎች እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1፡- የተለያዩ መጠን ያላቸው ፊላንጅዲ ፓይፕ ፊቲንግ እና የተለያዩ እቃዎች
  • ሎት 2:- የተለያዩ ውፍረት እና ስፋት ያላቸው አጠቃላይ ርዝመቱ 13,375 የሆነ ኤች ዲ ፕ ኢ (HDPE) ፓይፕ
  • ሎት 3:- ጀኔረተር 10KVA፤የኤችዲፒሲ መበያጃ፤ኮንክሪት ሚክሰር 350L ኮንክሪት ቫይብሬተር ከሆዝ ጋር እና የእንጨት እና የብረት መጋዝ

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት/TIN/ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ማንኛውም ተጫራች ያቀረበው ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው::CPO ለብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው።
  4. ለእያንዳንዱ ሎት ለጨረታ ሰነድ  መግዣ የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር/ በባንክ ሂሳብ ቁጥር 0439256067021/0439256067011/ ዳሽን ባንክ በመክፈል ከድርጅቱ ከግዥ ዋና ክፍል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
  5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ በኢትዮጵያ ብር መሆን አለበት።
  6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም:: እቃው የሚያቀርቡበት ቀንና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት።
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 05 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ:: ጨረታው ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ ከሰዓት 9፡00 ሰዓት በግዥ ዋና ክፍል ቢሮ ይከፈታል።
  8. ተጫራቾች የቴክኒካል ኘሮፖዛልና ፋይናሽያስ ኘሮፖዛል ለየብቻ በፖስታ አሽጎ ማስገባት አለባቸው።
  9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።

አድራሻ፤ ሰሚት ፋርማኪዩር አጠገብ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911475936/0913355890

ሚድሮክ ጂኦ ኤክስፕሎሬሽን አገልግሎት ኃ.የተ.የግ.ማ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-11
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid opening: 2026-08-11 15:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Midroc Geo- Exploration Services P.L.C.
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Reporter (Jul 29, 2026)
  • Posted at: 2026-07-29T14:45:48.000Z
← Back to all tenders