Pipes, valves and fittings

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በድሬድዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ኮንክሪት ፓይፕ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በድሬድዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት እየተሰራ ለሚገኘው ለቶጎጫሌ የመንገድ ስራ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በዝርዝር የተገለፀውን ኮንክሪት ፓይፕ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

/

የዕቃው አይነት

መለኪያ

ብዛት

የማስረከቢያ ቦታ

ምርመራ

1

ኮንክሪት ፓይፕ

ባለ 48 ኢንች

በቁጥር

 

3,500.00

ከጅጅጋ ከተማ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የፕሮጀክቱ ካምፕ

 

  • ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰአት የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ) ብር በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000322267979 ገቢ በማድረግ ድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ቢሮ ግዥ ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል
  • ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎች ባለስልጣን ማቅረብ አለባቸው
  • በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በመንግስት የዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት በኤጀንሲው ድረ ገጽ የተመዘገቡበትን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር )በባንክ ሲፒኦ ወይም ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  • ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ይዘጋል በዚሁ እለትም ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አካባቢ በሚገኘው በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ ፡-

  • ስለ ተፈለገው ኮንክሪት ፓይፕ ዝርዝር (ሙሉ) መረጃ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡

ስልክ ቁጥር 025111-13-13 /0927636126/0919008017

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

የድሬድዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-13
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-08-13 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Ethiopian Roads Administration Dire Dawa Road Maintenance District
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 27, 2026)
  • Posted at: 2026-07-27T09:11:35.000Z
← Back to all tenders