የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ኮተቤ ሳሊተምህረት አካባቢ ባለው የተቋሙ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ግንባታ ሳይት ላይ ተከማችቶ የሚገኘውን የግንበኛ ድንጋይ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የድንጋይ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤትኮተቤ ሳሊተምህረት አካባቢ ባለው የተቋሙ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ግንባታ ሳይት ላይ ተከማችቶ የሚገኘውን የግንበኛ ድንጋይ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ማንኛውም ለግንበኛ የሚሆን ድንጋይ መግዛት የሚፈልግ (ገዥ) ከዚህ በታችየተዘረዘሩትን በማየት መግዛት ይችላል።

1. የአንድ መኪና ቢያጆ የሽያጭ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ጨምሮ ብር 4,800.00 (አራት ሺ ስምንት መቶ ብር) ስለሆነ ገዥው ቢያንስ 05 /አምስት/ ቢያጆ እና ከዛ በላይ ብዛት መግዛት ይችላል።

2. ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአንድ መኪና ቢያጆ የሽያጭ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ጨምሮ በብር 4,800.00 (አራት ሺ ስምንት መቶ ብር) የ05 /አምስት/ እና ከዛ በላይ ቢያጆ አጠቃላይ ዋጋ በEEU-UEAP A/C No 1000-604742556 ገቢ በማድረግ የኢ.ኤ.አ. ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ከካቴድራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከኤንሪኮ ኬክ ቤት 150 ሜትር ርቀት በሚገኘው ዋስትና ንግድ ማዕከል ህንፃ ላይ 11ኛ ፎቅ በመቅረብ ደረሰኝ ማስቆረጥ ይችላሉ።

3. ገዥዎች የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት 7፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ኮተቤ አካባቢ ባለው የተቋሙ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ግንባታ ሳይት ድንጋዩን የሚጭን መኪና በማቅረብ ድንጋዩን አስጭነው መውሰድ ይችላሉ።

4. ድንጋዩን በተጫራች መኪና ላይ የመጫን ኃላፍነት የሻጭ ነው።

5. ድንጋዩን የሚጭን መኪና የማቅረብ ኃላፍነት የገዥ ነው።

6. ገዥ መግዛት የሚችለው ዝቅተኛው የቢያጆ መጠን 05/አምስት/ ነው።

7. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-126 3153 መደወል ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-13
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
  • Bid opening: 2026-07-13 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopia Electric Utility Project Portfolio Management Bureau
  • Published: Jun 27, 2026
  • Posted at: 2026-06-27T08:02:49.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders