የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በእስቶር የሚገኙ በጥቅል እና በኪሎ የሚሸጡ የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ ያገለገሉ እቃዎች
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ፍቢ002/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በእስቶር የሚገኙ በጥቅል እና በኪሎ የሚሸጡ
1ኛ. የተለያዩ የወንበር አይነቶች በጥቅል (የኃላፊ ወንበር፣ የባለሙያ ተሽከርካሪ ወንበር፣ የእንግዳ ወንበር)፣... ወዘተ
2ኛ.የተለያዩ የእንጨት ውጤቶች በጥቅል (የተሰበረ የባለሙያ ጠረጴዛ፣ የጠረጴዛ አክሰሰሪ ጣውላዎች፣ የኃላፊ ጠረጴዛ ጣውላዎች፣ ወዘተ
3ኛ. የፕላስቲክ ውጤቶች በጥቅል( የቆሻሻ ማፈሻ፣ የሽንት ቤት ብሩሽ፣ የወረቀት ትሪ፣...ወዘተ
4ኛ የኤሌክትሪክ እቃዎች በጥቅል( ፍሎረሰንት ማቀፊያዎች ትልቁና ትንሹ፣ የሽንት ቤት የስልክ ቀፎ .ወዘተ...
5ኛ የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች ዲቪዲዎች፣ ሲዲዎች፣ የብዕር ቀለም በጥቅል እና ነጋሪት ጋዜጦች በኪሎ
6ኛ የቆርቆሮ ውጤቶች በጥቅል ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎች፣ የቀለም ጣሳዎች፣ የኤርፍሬሽነር ጣሳዎች በጥቅል የሚሸጡ በማለት የለያቸውን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ለመወዳደር የሚያስፈልጉ
- ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ሰነድ የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር በመግዛት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ /10/ አስር ቀናት ውስጥ በግዥ ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት በመገኘት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃውን 2% ማስያዝ አለባቸው። ያለፉበትን እቃ በጊዜ የማያነሱ ከሆነ የጠቅላላ ዋጋውን 0.01% በየቀኑ እየተሰላ በመቀጫነት እንዲከፍሉ ይደረጋል። ሆኖም የመቀጫው መጠን የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲደርስ ያስያዙት ጨረታ ማስከበሪያ ለቢሮው ገቢተደርጎ አሸናፊነቱ ይሰረዛል።
- አሸናፊዎች ማለፋቸው በተገለፀላቸው 5 /አምስት/ቀናትውስጥ በጥቅሉ የተገለፁትን እቃዎች በሙሉ ማንሳት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ በማስገባት በ11ኛው ቀን 3፡00 /ሶስት/ ሰአት ተዘግቶ 3፡30 (ሶስት ተኩል) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እለት ይከፈታል፡፡
- ቢሮው ጨረታውን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ ንገድ ካገኘ ታውን ሙ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ሜክሲኮ ሰነዱ የሚሸጠው ፊሊፕስ ህንፃ አጠገብ ፍትህ ቢሮ ህንፃ ከፌዴራል ፖሊስ ወረድ ብሎ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ህንፃ 4ኛ ወለል ላይ ይሆናል።
ስልክ ቁጥር፦ 0115 159 54
ማሳሰቢያ፦ ተጫራቾች ዕቃውን በአካል በመገኘት ማየት ይኖርባቸዋል። በጥቅል ለተሰጡ ዕቃዎች ለይቶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-07-07
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 3፡00 /ሶስት/ ሰአት
- Bid opening: 2026-07-07 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 3፡30 /ሶስት ተኩል/ ሰአት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Justice Office
- Buyer address: ሜክሲኮ ፈሊፕስ አጠገብ ወይም ጨለለቅ አልሳም ታወር ፊት ለፊት
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jun 27, 2026
- Posted at: 2026-06-27T08:36:44.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.