የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ ብረት በር፣ አልሙንየም እና የእንጨት ፓሌቶች ፍላጎት ላላቸው ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ

ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ ብረት በር፣ አልሙንየም እና የእንጨት ፓሌቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አቃቂ በሚገኘው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ጥናት ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ፣ብረት በር ፣ አልሙንየም እና የእንጨት ፓሌቶች ፍላጎት ላላቸው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ተ.እ.ታ) ተመዝጋቢ ሆኖ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ንግድ ምዝገባ፤ ታክስ ምዝገባ ሠርቲፊኬት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ጊዜ ያላለፈበት ታክስ ክሊራንስ ሠርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ ለሆኑ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ፡-

  1. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ወቅት የድርጅቱን መታወቂያ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በባንኩ ህንፃ ቁጥር 2 ምድር ቤት ላይ በሚገኘው ባንኪንግ እና ፐይመንት ሲስተምስ ዳይሬክቶሬት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስም በሂሳብ ቁጥር 7002010800001 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ በህንፃ ቁጥር 2 2ኛ ፎቅ ፋሲሊቲ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ለጨረታው መረጃ ማግኘትና የጨረታውን ሰነድ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ጨረታውን ለመሳተፍ ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ የእንጨት ፓሌቶች ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺ ብር) ፣ብረታ ብረቶች፤ አልሙንየም ብር 50,000.00 (ብር ሃምሳ ሺ) እና ብረት በር ብር 20,000 (ሃያ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቢድ ቦንድ (ሲ.ፒ.ኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት ክፍል የበር መግቢያ ፍቃድ በመውሰድ እና የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ንብረቶቹን ባሉበት ቦታ ማየት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ ብረት በር፣ አልሙንየም እና የእንጨት ፓሌቶች የሚገዙበትን ዋጋ በዋጋ ማስረከቢያ ቅፅ ላይ በማካተት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ሙሉ አድራሻውን እና የጨረታውን ቁጥር በመጥቀስ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በህንፃ ቁጥር 2 ሁለተኛ ፎቅ ፋሲሊቲ ዳይሬክቶሬት ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ይከፈታል።
  7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ

በስልክ ቁጥር፡-  011 517 5191/ 011 517 5193/ 011 517 5223

ደውሎ መጠየቅ ይችላል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-13
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-07-13 10:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: National Bank of Ethiopia
  • Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jun 28, 2026
  • Posted at: 2026-06-29T08:51:15.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders