ብርሃን ባንክ አ.ማ. ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ጃኬት ለመግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የጃኬት ግዥ ጨረታ

አገር አቀፍ የግልጽ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር ብ/ባ/ግጨ/ደል/20256/27/02

  1. ብርሃን ባንክ በ2018 በጀት ዓመት ለሰራተኛች አገልግሎት የሚውል ጃኬት ግዥ ለማከናወን በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የብር 100,000.00 (ብር አንድ መቶ ሺ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) መልክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ  እሴት ታክስ ከፋይ የምስክር ወረቀት እና የታክስን ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 345.00 (ብር ሦስት መቶ አርባ አምስት) በማንኛውም የብርሃን ባንክ አማ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈጽመው ደረሰኙን በማቅረብ ከባንኩ ዋና መ/ቤት ከሚገኝበት ቦሌ ድልድይ ወመሳድኮ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ከሰፕላይ ቼን እና ውል አስተዳደር መምሪያ ቢሮ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ህጋዊ ሰነዶችና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሰነድ በአንድ ፖስታ እና የዋጋ ሰነድ በሁለተኛ ፖስታ በዋና እና በኮፒ ማቅረብ ሲኖርባቸው ለሚሳተፉበት ጃኬት ናሙና ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ሀምሌ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በባንኩ ዋና መ/ቤት በሚገኝው ቦሌ ድልድይ ወመሳኮድ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ከሰፕላይ ቼን እና ውል አስተዳደር መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  7. ጨረታው ሀምሌ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተገለጸው ቢሮ ይከፈታል።
  8. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኝ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።

ብርሃን ባንክ አ.ማ.

ከሰፕላይ ቼን እና ውል አስተዳደር መምሪያ

ስልክ ቁጥር 011 663 2097/ 011 650 7422


Tender details

  • Deadline: 2026-07-14
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-07-14 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Berhan Bank S.C.
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 345.00 ብር
  • Published: Jun 28, 2026
  • Posted at: 2026-06-30T04:54:12.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders