የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጡረተኞች ማህበር ከሐምሌ 01 ቀን 2017 ዓ.ም. በጀት ዓመት ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ተከታታይ የበጀት ዓመታት ሂሳቡን ለማስመርመር ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል

Description

የኦዲት ሥራ ባለሙያ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጡረተኞች ማህበር ከሐምሌ 01 ቀን 2017 ዓ.ም. በጀት ዓመት ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ተከታታይ የበጀት ዓመታት ሂሳቡን ለማስመርመር (ኦዲት ለማስደረግ) ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ የኦዲት ተቋማት አወዳድሮ አሸናፊውን መምረጥ ይፈልጋል።

መሟላት የሚገባቸው መሥፈርቶች

  • በአዋጅ ቁጥር 847/2006 አንቀጽ18 መሠረት የኦዲት ሙያ ማረጋገጫ ያለውና በመንግሥት የተመዘገበ፣
  • በኦዲት ሥራ በቂ ልምድ ያለው፣
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፣
  • ከአሁን በፊት ኦዲት ያደረጋቸውን ድርጅቶች ዝርዝር ማቅረብ የሚችል፣

ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) የስራ ቀናት ውስጥ የምትሰሩበትን ዋጋ እና ሥራውን ሠርታችሁ የምታቀርቡበትን ጊዜ በመጥቀስ ደረጃችሁን እና ሕጋዊነታችሁን የሚገልጽ ማስረጃዎቻችሁን በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከታች በተጠቀሰው አድራሻ በማመልከት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።

አድራሻ፡- ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋናው መስሪያ ቤት ግቢ ውስጥ ነው።
የስልክ ቁጥር፡- 011 517-8283 /011 517-8753 ሞባይል፣ 09 37-92-96-03
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጡረተኞች ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-07-10
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) የስራ ቀናት ውስጥ
  • Bid opening: 2026-07-10 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰአት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጡረተኞች ማህበር
  • Published: Jun 30, 2026
  • Posted at: 2026-06-30T14:02:31.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders