በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ስኳር ኢዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ከግንባታ የተራረፉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሽያጭ ጨረታ ቁጥር- አሸጨ 001 /ኦኩስፋ /ቁ-2/2018

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ስኳር ኢዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ሎት 1 - ከግንባታ የተራረፉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት 100 ቶን ሸያጭ ጨረታ

ስለዚህ፡-

1. በዘርፉ የተሰማራችሁና በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ የቫት ምዝገባ ሰርተፊኬት እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

2. በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ) ከሰዓት በፊት ከ2፡30 – 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30 – 6፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤምቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ/ በባንክ የተመሰከረለት (CPO) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

5. ተጫራች ለተጫረተው ዕቃ መነሻ ዋጋ መሰረት ለመግዛት በቂ አቅም መኖሩን ለማረጋገጥ የባንክ ስቴትመንት ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6. ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።

7. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 60 ቀናት ነው።

8. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተከታታይ 60 ቀናት ነው።

9. የዕቃው ርክክብ የሚፈፀመው ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ የሚገኝበት ማለትም ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ኃይል ውሃ ቀበሌ ነው።

10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ይሆናል።

አድራሻ፡- ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አዲስ አበባ ነው።

ለበለጠ መረጃ ይህንን የስልክ ቁጥር መጠቀም ይቻላል 09 91 14 94 85 / 09 40 20 94 64

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስኳር ኢዱስትሪ ግሩፕ
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-15
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-07-15 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Omo Kuraz No-2 Sugar Factory
  • Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: ብር 300.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Jun 30, 2026
  • Posted at: 2026-06-30T14:11:45.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders