የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ 17 ዓይነት የዲስትሪቢዩሽን ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ንአ/ግጨ-09/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የሚወገደው ንብረት ዓይነት |
የሚገኝበት ቦታ |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታ መዝጊያ |
የጨረታ መክፈቻ |
|
1 |
የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች |
ኮተቤ ጋራዥ |
በቁጥር |
42 |
የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20% |
ሀምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 |
ሀምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 |
|
2 |
17 ዓይነት የዲስትሪቢዩሽን ዕቃዎች |
ጎፋ ዕቃ ግምጃ ቤት
|
በኪ.ግ
|
6,973.29
|
35,000
|
ሀምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 |
ሀምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 |
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡- ውድድሩ የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ በኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር በፈጠሩት የማወዳደሪያ ሲስተም መተግበሪያ auction.et መሰረት መሆኑን እየገለጽን፤ መስፈርቶቹ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነትያላቸውሆኖይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሠ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል።
- ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ በነጻ አውርደው መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ጋር ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና(Bid Security) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስም ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ።
- ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
- በጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ ከሚገለፅበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ክፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት የመፈጸም ግዴታ ይኖርባችኋል፤ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለወድድር ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል።
- ከላይ የተጠቀሰውን እና በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ሊደረግ ይችላል።
- ተቋሙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-55-11 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- ንብረቶቹን በተመለከተ በስልክ ቁጥር 011-1-11-98-97 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
Tender details
- Deadline: 2026-07-23
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-07-23 14:30
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published: Jul 01, 2026
- Posted at: 2026-07-01T07:38:22.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.