Disposal, scrap and surplus sales
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ፤ የተለያዩ የሚወገዱ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ፤ የተለያዩ የሚወገዱ ንብረቶችን፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን ሊያሟሉ የሚችሉ ፈላጊዎች መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)፤ በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ.ፒ.አ (CPO ) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፤
- የጨረታ ሰነዱን፤ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ፣ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ ፤ ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርበው፣ ብር 500 (አምስት መቶ ብር)፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በከተማ አስተዳደሩ አካውንት ገቢ በማድረግ፣ መግዛት እና ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ፤ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (ለአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ወይም እስከ መጨረሻ ጨረታ መዝጊያ ሰዓት 3፡30 ድረስ በፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዥ ኬዝ ቲም )፤ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ፣ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ በሌሉበት በዕለቱ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የበዓል ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን፣ በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።
- በጨረታ ማስታወቂያ እና በጨረታ ሰነዱ ላይ የቃላት እና የቁጥር ልዩነቶች የሚያጋጥም ከሆነ፤ በጨረታ ሰነዱ ላይ ላለው በላይነት ይኖረዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ/ሀዋሳ/
Tender details
- Deadline: 2026-07-16
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-16 10:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau
- Bid bond: 200,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jul 01, 2026)
- Posted at: 2026-07-01T07:42:09.000Z