የገቢዎች ሚኒስቴር የተለያየ ሞዴል ያላቸው 4 ተሽከርካሪዎችን እና የሞተር ሣይክል ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ዕዳ የያዛቸውን የተለያዩ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎችንና የሞተር ሣይክል ለመሽጥ የመጣ የግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁ- 06/2018

የሚኒስቴር መ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በታከስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ከምቾት ዳይፕር ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ ከኤድናሞል EHTS ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ካልሜ ኃ/ የተ/የግ/ማህበር የተያዙ የተለያየ ሞዴል ያላቸው 4 ተሽከርካሪዎችን እና ከኤ.ዋይ.ቢ.ኤ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር የተያዘ የሞተር ሣይክል ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

1. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ(ፓስፖርት) ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ በማሸግ ለግልፅ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00ሰዓት ህንፃ “መ” 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 ከግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ህንፃ “ሀ” 2ኛፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ከታከስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይኖርበታል።

3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ 1/10ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር ስም (Minstry of Revenue) በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ።

.

 

የመ/ቤቱ ስም

 

ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት

የንብረቶቹ መመልከቻ ቀን

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

 

ገቢዎች ሚኒስቴር

 

የተለያየ ሞዴል ያላቸውተሸከርካሪዎች

 

ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀናት

 

ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16 ቀን 345 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 400 ሰአት ይከፈታል።

5. የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡- መገናኛ በሚገኘው በሚኒስቴር መ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቶች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።

6. የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል።

7. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልፅ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

8. የተሸከርካሪ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ-ንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች (የቦሎና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎች ሻጭን አይመለከትም።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤቱ በሚሠጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፋበትን ሀብት/ንብረት መረከብ ይኖርባቸዋል።

10. ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልፅ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በCPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንዳልተሸጠ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

11. ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልፅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 617-84-90 ኮድ (2044)(2045)(2046) የውስጥ
መስመር (EXT) 2044 ደውለው መጠቅ ወይም የተቋሙን ዌብሳይት WWW.MOR.Gov.et   መመልከት ይቻላል።
ገቢዎች ሚኒስቴር


Tender details

  • Deadline: 2026-07-16
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 3፡45
  • Bid opening: 2026-07-16 12:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 4፡00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ministry of Revenue
  • Buyer address: የቀድሞ ቡና ቦርድ ከንፋስ ስልክ ት/ቤት ዝቅ ብሎ ባለው ሙለጌ ህንፃ ላይ
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published: Jul 01, 2026
  • Posted at: 2026-07-01T08:17:45.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders