የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የውጭ ኦዲተሮችን አወዳድሮ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ሂሳብ ማስመርመር (ኦዲት ማስደረግ) ይፈልጋል
Description
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር
የውጭ ኦዲተር የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር AGPBTU/01/2018
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የውጭ ኦዲተሮችን አወዳድሮ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ሂሳብ ማስመርመር (ኦዲት ማስደረግ) ይፈልጋል።
ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ኦዲተሮች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችል የሙያ ፍቃድ ያገኘና የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
- የኦዲት ሥራ ለመሥራት የሚያስችል ወቅታዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ/የሆነች፣
- የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው/ያላት፣
- ተጫራቾች የአገልግሎት ክፍያ የዋጋ ዝርዝር ጠቅላላ ዋጋቸውን ታክስን ጨምሮ እና ሥራውን ሠርተው የሚያጠናቅቁበትን ጊዜ ማለትም የሂሳብ ምርመራውን አጠናቅቀው ዘገባውን (Report) የሚያስረከቡበትን ጊዜና በሙያዉ ያላቸዉን ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችና ዝርዝር ሁኔታዎችን በመሙላት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስርያ ቤት ግቢ ዉስጥ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሰረታዊ የሠራተኛ ማህበር ጽ/ቤት በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለ3 የስራ ቀን የሚቆይ ሲሆን ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት በማህበሩ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ከዚህ በታች በተቀመጠው ስልክ ቁጥር መጠየቅ ይችላሉ።
011 657 1471/ 011 517 8451/ 011 517 8951
Tender details
- Deadline: 2026-07-03
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-07-06 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር
- Published: Jul 01, 2026
- Posted at: 2026-07-01T09:07:24.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.