External audit and assurance
ኩል ፍረሽ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት አጠቃላይ የሒሳብ መዝገቡን በታወቀ እና እውቅና ባለው የውጭ ኦዲት (External Audit) ድርጅት ማሰራት ይፈልጋል
Major contract
External audit and assuranceAccounting and Auditing, Accounting System DesignAmharic
Addis Ababa
Description
የውጭ ኦዲት አገልግሎት ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ኩል ፍረሽ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ከአርብቶ አደሩ ጥሬ ወተት በመሰብሰብ ለአቀነባባሪዎች በማቅረብ ስራ ላይ የተሰማራ ድርጅት ነው። ድርጅታችን የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት አጠቃላይ የሒሳብ መዝገቡን በታወቀ እና እውቅና ባለው የውጭ ኦዲት (External Audit) ድርጅት ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ የኦዲት ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን።
1. ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች፡
- የታደሰ የ 2018 ዓ.ም የንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ (AABE) የተሰጠ እና የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የሂሳብ መዝገቡን በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች (IFRS) መሠረት ኦዲት የማድረግ በቂ ልምድ ያላቸው፤
- ስራውን አጠናቀው የኦዲት ሪፖርት የሚያስረክቡበትን ትክክለኛ ጊዜ (Timeframe) መግለጽ የሚችሉ።
2. የጨረታ አቀራረብ መመሪያ፡
- ተጫራቾች የቴክኒክ (Technical) እና የፋይናንስ (Financial) ሰነዶቻቸውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የቴክኒክ ሰነድ፡ የድርጅቱን መገለጫ (Profile)፣ የህጋዊነት ማስረጃዎችን እና የተመደቡ ባለሙያዎችን የትምህርትና ስራ ልምድ (CV) ማካተት አለበት።
- የፋይናንስ ሰነድ፡ ለአገልግሎቱ የሚጠይቁትን ጠቅላላ ዋጋ (ሁሉንም ታክሶች ጨምሮ) በግልጽ ማሳየት አለበት።
3. የጨረታ ማመልከቻ ጊዜ እና ቦታ፡
- የማመልከቻ ማብቂያ ቀን፡ ተጫራቾች መረጃዎቻቸውን በሙሉ በማሟላት እስከ ሀምሌ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ማመልከት ይችላሉ።
- የማስረከቢያ ቦታ፡ ከተማ አዲስ አበባ ክ/ከተማ የካ / ልዩ ቦታ ጉርድ ሾላ ሳሊተምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ድራር ሞል ህንፃ 7ኛ ፎቅ
- ማሳሰቢያ፦ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ እና ማመልከቻ ማስገቢያ አድራሻ፡
- ስልክ ቁጥር: 0961252431/0903383840 ኢሜይል: [email protected] / [email protected]
- አድራሻ: ከተማ አዲስ አበባ ክ/ከተማ የካ / ልዩ ቦታ ጉርድ ሾላ ሳሊተምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ድራር ሞል ህንፃ 7ኛ ፎቅ
Tender details
- Deadline: 2026-07-12
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-07-12 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Cool Fresh Agro Processing PLC
- Buyer TIN: 0083398879
- Published on: 2merkato.com (Jul 01, 2026)
- Posted at: 2026-07-01T11:10:32.000Z