የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለሚገነባቸው የተለያዩ ግንባታ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል ሲሚንቶ ከለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ እንዲሁም የግንባታ ብረት ከባ/ዳር፣ ከአዳማ፣ ከገላን፣ ከሸኖ እና ከቢሾፍቱ ከተሞች ከሚገኙ ፋብሪካዎች ፕሮጀክቶች ወዳሉበት ከተሞች ስሚንቶ እና ብረት ለማጓጓዝ ይፈልጋል
Description
የሲሚንቶ እና ብረት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ግልጽ
የጨረታ ቁጥር ዘመን/ማሽግ/ 01/2019
የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለሚገነባቸው የተለያዩ ግንባታ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል ሲሚንቶ ከለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ እንዲሁም የግንባታ ብረት ከባ/ዳር፣ ከአዳማ፣ ከገላን፣ ከሸኖ እና ከቢሾፍቱ ከተሞች ከሚገኙ ፋብሪካዎች ፕሮጀክቶች ወዳሉበት ከተሞች ስሚንቶ እና ብረት ለማጓጓዝ ለመፈጸም ይፈልጋል።
ህጋዊ ከሆኑና ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
1- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፋቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም የባለቤትነት መታወቂያ ሊብሬ ያላቸው
2- የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ድርጅት ቀበሌ 11 ኮብል አክሲዮን ማህበር ፊት ለፊት ወደ ዲያስፖራ በሚወስደው መንገድ በሚገኘው የድርጅቱ ህንጻእና አ/አበባ ለገሀር አመልድ ኢትዮጵያ ህንጻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘዉ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በመገኘት የማይመለስ 500 ብር ከፍሎ መውሰድ ይችላል።
3- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ተናት ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ብቻ ባህር ዳር ከተማ በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ድርጅት ቀበሌ 11 ኮብል አክሲዮን ማህበር ፊት ለፊት ወደ ዲያስፖራ በሚወስደው መንገድ በሚገኘው የድርጅቱ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 109 በጀት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል.
4- ጨረታው በ15ኛው ቀን 8፡00 ይዘጋና በዚያኑ ቀን 8፡30 ይከፈታል። 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ በዚያው ቀን 8፡00 ተዘግቶ 8፡30 ይከፈታል።
5- ዝርዝር የጨረታ መመሪያን እና የውል ይዘቱን እንዲሁም የሚገዙትን አገልግሎቶች ከጨረታ ሰነዱ በዝርዝር የተገለፀ ስለሆነ ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት መሞላት አለበት።
6- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
7- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው.
ስልክ ቁጥር 058 218 0538/ 09 27 60 55 99/ 09 18 30 59 49/ 09 18 81 67 32/ 09 39 23 03 03
ባህርዳር
የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-07-16
- Publishing entity: ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
- Bid bond: 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: Jul 02, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.