በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የተተው ዕቃዎች የሀራጅ ጨረታ ቁጥር ሐ_47/2018 የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት አስመጭዎች ዕቃቸዉን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተዉ የተቆጠሩ እና በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 10 መሠረት የተተዉ ንብረቶችን ማለትም AC ADAPTOR, HD TV CABLE FOLDABLE KID MINI LAPTOP TABLET TV WALL MOUNT LED HIGHBAY LIGHT HAND WATCH WOODEN DOOR FRAME & WATER PURIFIER OUT DOOR SOLAR STRIGHT LIGHT & STRIGHT LIGHT STAND LED STRING LIGHTS: RUBBER NAIL FILTER, S/S MANICURE, METAL DECORATIVE & EYE LASH I PHOTO COPY MACHINENERY AND PRINTER ADULT FABRIC CAP, SHOPPING BAG & OTHERS! RECHARGEBLE CAMPING PORTABLE SHOWER WALL TRANSFORMERI CHEMICAL MIXING TANK, CHANNEL STEEL, GALVANISED STEEEL PIPE & OTHERS! HEALD FRAME FABRIC MICRO FIBER CLEANING TOWELI WIRE PROFESSIONAL HOTEL SPECFLC TELEPHONE: RELIGIOUS BOOKS COMPLET SET DOUBLE LEAF STEEL FRE HATED DOOR CHEFON MATERIAL የተለያዩ የህክምና መገልገያ እቃዎች SINGLE DOUBLE PORT FACE PLATE & Others/S ARTIFICIAL EARRING & BEARING CHILDREN FROCK, BABY FROCK, LADY OPEN SHOES, LADY IMITATION SHOES & OTHER እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሱ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1) ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት በማስታወቂያ ሠሌዳ እና በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 መመልከት ይቻላል።

2) ተጫራቾች በጨረታ ከሚሽጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000,00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።

3) ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበት በዘርፉ በረደው ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋጢ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል። ተጫራቾች የሚያዙት CPO በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፣ አዳማና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት።

4) የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኃላ በ6ኛው የሥራ ቀን በዚሁ ዕለት ጠዋት 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ የሚከፈት ሆኖ ማንኛውም ተጫራች እስከ 4፡45 ሰዓት የሚጫረትበትን ዕቃ ለይቶ እቃ አወጋገድ ቡድን ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል።

5) ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድርማግለል አይቻልም፤ የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

6) የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት። በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

7) በተራ ቁጥር 06 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።

8) አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።

9) ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10) ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 022-236-9094 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-07
  • Publishing entity: Ethiopian's Customs Commission Modjo Branch Office
  • Bid bond: 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር)
  • Published: Jul 02, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders