የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ያገለገሉ የሬንጅ በርሜሎች፣ የሬንጅ በርሜሎች ከነክዳናቸው እና የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የተቆራረጡ ቆርቆሮዎች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

 የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት የሆነ የመንገዶች ባለስልጣን

  • ያገለገሉ የሬንጅ በርሜሎች፣
  • የሬንጅ በርሜሎች ከነክዳናቸው እና
  • የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የተቆራረጡ ቆርቆሮዎች

 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች ከአፍንጮ በር ወደ 6 ኪሎ በሚወስደው መንገድ ፍቅር ፕላዛ ህንፃ ላይ በሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመምጣት የተለያዩ ተቋማት የመንገዶች ባለስልጣን ያገለገሉ የሬንጅ በርሜሎች፣ የሬንጅ በርሜሎች ከነክዳናቸው እና የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የተቆራረጡ ቆርቆሮዎች ለእያንዳንዱ ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ተገኝተው መግዛት ይችላሉ።
  2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር ዋጋ በአሃዝ እንዲሁም በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402 ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚታሸግበት ሰዓት ድረስ ተጫራቶች ሰነድን ማስገባት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች በአሃዝና በፊደል እንዲሁም በነጠላና በጥቅል በሰጡት ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ አገልገሎቱ ከፍተኛውን ዋጋ ወስዶ ያወዳድራል።
  4. ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በመግለጽ በመጫረቻ ሠነዳቸው ላይ መፈረም አለባቸው።
  5. ተጫራቾች በአንድ መለያ ቁጥር(መደብ) ስር ያለውን ንብረት ብዛት በሙሉ መጫረት አለባቸው፤
  6. ተጫራቾች ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ድረስ በመሄድ ንብረቱን አይተው መጫረት ወይም ዋጋ መስጠት አለባቸው። ነገር ግን ንብረቱን ሳያዩ ቢጫረቱና ቅሬታ ቢቀርብ አገልግሎቱ ሀላፊነቱን አይወስድም።
  7. ለሚገዙት የተለያዩ ተቋማት ያገለገሉ የሬንጅ በርሜሎች፣ የሬንጅ በርሜሎች ከነክዳናቸው እና የተቆራረጡ ቆርቆሮዎች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 10 በመቶ (10%) እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ሲ.ፒ.ኦ. ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
  8. የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 504 ይከፈታል። ሆኖም የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል።
  9. ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም።
  10. በመነሻ ዋጋና በታች የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።
  11. የጨረታ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ ኮድ ወይም መለያ ቁጥር ሲጽፍ ተሳስቻለሁ ወይም ሳልጽፍ ቀርቻለሁ የሚሉ ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸውም።
  12. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለአገልግሎቱ ገቢ ይደረጋል።
  13. ንብረቱን በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
  14. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ ከጨረታው መውጣት ወይም የሰጠውን ዋጋ ማሻሻል ወይም መለወጥ አይችልም።
  15. የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ማናቸውም ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-557-8671 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አገልገሎቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-17
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-17 10:15
  • Bid opening (note): የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡15 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Administration Public Procurement and Property Disposal Service
  • Buyer address: Mexico Sengatera, behind St. Mary University College, located at Yobek Commercial center.
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published: Jul 02, 2026
  • Posted at: 2026-07-02T07:35:54.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders