የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡-ኢፕድ 026/2018
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በዉድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።
1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታከስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸዉ።
2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ግዥዉን አስመልክቶ የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምርያ በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመዉሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ4 በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸዉን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀዉ አንደኛ ፎቅ በሚገኘዉ አቅርቦት መምሪያ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ።
3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበርያ የሚዉል ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /ቢድ ቦንድ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡ ሆኖም ግን በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አካላት ከአደራጃቸዉ አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባነይት ይኖረዋል
4. ጨረታዉ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚዉል ሲሆን በ16ኛዉ የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አንደኛ ፎቅ በአቅርቦት መምርያ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለዉ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ኢሜይል procurement@press.et
አድራሻ፡ አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም መተሚያ ድርጅት ፊትለፊት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-07-18
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-07-18 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሠዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Press Agency
- Buyer address: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published: Jul 03, 2026
- Posted at: 2026-07-03T07:16:11.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.