በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮችን ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ሸልፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢንዱስትሪያችን ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮችን ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ሸልፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ስለሚፈልግ ማንኛውም ተወዳዳሪ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት (10) አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዋጋ በማስገባት መወዳደር የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን።
ተወዳዳሪዎች ከታች የተዘረዘሩት መመሪያዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. ማንኛውም ተወዳዳሪ የሚቀርበው ዋጋ በታሸገ ፖስታ መሆኑን ማረጋገጥና በኢንዱስትሪው ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅበታል። ፖስታው ላይ የባለቤቱ ፊርማ መፈረም ይኖርበታል።
2. ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ወይንም ፓስፖርት ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አብሮ ማቅረብ ይኖርበታል።
3. ተጫራቾች ጨረታውን ለመወዳደር የ5,000 (አምስት ሺህ) ባንክ ሲፒኦ ከጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅበታል።
4. ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋ ላይ ቅሬታ ካላቸው ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ቅሬታቸውን በጽሁፍ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከተገለፀው ቀን በኋላ የሚመጣ ቅሬታ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እንገልፃለን።
5. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን 10ኛው ቀን ላይ ጠዋት 4፡00 ሰአት ላይ ጨረታው ተዘግቶ በዛው ቀን ከጠዋት 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች አለመገኘታቸው ጨረታውን ከመከፈት የማያግደው መሆኑን እናሳውቃለን።
አድራሻ፡- ከመገናኛ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ ኒያላ ሞተርስ ፊት ለፊት አንበሳ ጋራዥ አጠገብ ሲሆን
ስልክ ቁጥር 011 859 2286
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ
Tender details
- Deadline: 2026-07-14
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ10ኛው ቀን ላይ ጠዋት 4፡00 ሰአት
- Bid opening: 2026-07-14 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ10ኛው ቀን ላይ ከጠዋት 4:30 ሰአት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ
- Bid bond: 5,000.00 ብር
- Published: Jul 03, 2026
- Posted at: 2026-07-03T07:24:00.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.